Fana: At a Speed of Life!

በቡሌ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ቁሳቁስ በተሟላ ሁኔታ ደርሷል – የጌዲኦ ዞን ምርጫ አስተባባሪ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጌዲኦ ዞን ቡሌ ምርጫ ጣቢያ በነገዉ እለት በሚደረገዉ ምርጫ የቁሳቁስ ስርጭት በተሟላ መልኩ መጠናቀቁን የዞኑ የምርጫ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ አበባየሁ ገለጹ፡፡
ባለፈው ሰኔ ወር 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሲካሄድ በተለያዮ ምክኒያቶች በድጋሜ ምርጫ እንዲካሄድ ከተደረጉት ምርጫ ክልሎች መካከል 83 የምርጫ ጣቢያዎችን የያዘው የጌዲኦ ዞን የቡሌ ምርጫ ክልል ነገ ለሚየደረገው ምርጫ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የዞኑ የምርጫ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ አበባየሁ ተናግረዋል፡፡
ከ58 ሺህ በላይ መራጮች ካርድ መውሰዳቸውንም የጠቆሙት አስተባባሪዉ መራጮች በነገው ምርጫ በመሳተፍ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡም እና የፖለቲካ ፖርቲዎችም የተሰጣቸውን ድምጽ አክብረዉ በፀጋ እንዲቀበሉም አሳስበዋል፡፡
በታሪክነሽ ሴታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.