የኢሬቻ በዓልን ስናከብር ራሳችንን ከኮቪድ-19 በመጠበቅ መሆን እንደሚገባው አባገዳዎች አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓልን ስናከበር ራሳችንን ከኮቪድ-19 በመጠበቅ እና ፕሮቶኮሉን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት አባገዳዎች አሳስበዋል፡፡
አባጋዳዎቹ ይህን ያሉት ዛሬ ከሃደ ሲቄዎች እና ፎሌዎች ጋር ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡
በኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት ኮቪድ-19ን ለመከላከል መደረግ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ውይይት ተደርጓል፡፡
የበዓሉ ታዳሚዎች የኢሬቻ በዓልን ሊያከብሩ ከቤታቸው ከሚወጡበት ሰዓት ጀምሮ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን ማስክ ማድረግ፣ የእጅን ንፅህና መጠበቅ፣ በተቻለ መጠን ርቀትን በመጠበቅ መሆን አለበት ተብሏል፡፡
የኦሮሞ ፎሌዎችም በእለቱ የመከላከያ መንገዶችን ህብረተሰቡ እንዲከተል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
በዓሉ በሚከበርበት አከባቢ በሁሉም መዳረሻዎች ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ እና ለክትባት ፈላጊዎች አገልግሎት እንደሚሰጥም መገለጹን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!