Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ በሀረሪ ክልል መካሄድ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ዛሬ ለሚካሄደው ስደስተኛው ሀገራዊ ምርጫ መካሄድ ጀምሯል።

መራጩ ህዝብም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፅ እየሰጡ ይገኛል።

መራጮች በሰጡት አስተያየት በነፃነት ያለ ማንም ተፅዕኖና ድምጻቸውን ለሚፈለጉት አካል መስጠታቸውን ገልፀዋል።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተዘዋውሮ ምልከታ ባደረገባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የተለያዩ የሲቪስ ማህበራት የህዝብ ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት ሲታዘቡ ተመልክቷል።

በሀረሪ ክልል በሁለት የምርጫ ክልሎች በተቋቋሙ 229 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው መካሄድ የጀመረ ሲሆን 7 ፓርቲዎች እየተፎካከሩ ይገኛሉ።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.