Fana: At a Speed of Life!

የኛ ቲቪ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት እና ወቅቱን ያላገናዘበ ዘገባ ሰርቷል ለተባለው ለየኛ ቲቪ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
 
ባለስልጣኑ የኛ ቲቪ በተሰኘው ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ከዜጎች በቀረበ ጥቆማ እና በተደረገ ምርመራ መሰረት ማረጋገጥ እንደቻለ ገልጿል፡፡
 
በዚህ መነሻም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለቴሌቭዥን ጣቢያው የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
 
መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣኑ÷በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የመገናኛ ብዙኃን ሀሰተኛ መረጃ እና ወቅቱን ያላገናዘበ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ማሳሰቡን ከመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.