Fana: At a Speed of Life!

የሰላምና ልማት ማዕከል የተሰኘው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ፈቃድ ተሰረዘ

አዲስ አባበ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን አገር ለማፍረስ በድብቅ ሲወያዩ የነበሩትን የእነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅ፣ እሌኒገብረመድህ፣ አሸባሪው ብርሀነ ገብረክርስቶስ እና አጋሮቻቸውን ውይይት ያዘጋጀው የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰረዘ።
 
ይህ ማዕከል ሰሞኑን በፕሮፌሰር ኤፍሬም አወያይነት የቀድሞ የአሜሪከ አምባሳደሮችና የአሸባሪው ህወሓት አባላትና የጥቅም ተጋሪዎች የተካሄደው ኢትዮጵያን የማፍረስ ውይይት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 9 መሰረት፤ የአገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ የሚጠረጠር የሲቪል ማህበር ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ ያዛል በሚለው መሰረት የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰርዟል።
 
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ባለስልጣኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የማዕከሉ ፈቃድ እንዲሰረዝ በወሰነው በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 88/3 መሰረት በኤጀንሲው ዳግም ተመዝግቦ በምንዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥር 2936 ህጋዊ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ የቆየ መሆኑ ይታወሳል።
 
ይሁን እንጂ በአገር ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አዳጋ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀፅ 4 ንዑስ አንቀፅ 9 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የአገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል ተብሎ በተደነገገው መሰረት ከላይ በስም የተጠቀሰው ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ውሳኔ ያሳለፈ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር በቁጥር ፍ/ሚ-01/ባሰ-9/500773 ሕዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አሳውቋል፡፡
በዚሁም መሰረት የሰላምና ልማት ማዕከል የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የምዝገባ የምስክር ወረቀት (ፈቃድ) ከዛሬ ህዳር 17/2014 ጀምሮ የተሰረዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.