Fana: At a Speed of Life!

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ስንቅ እያዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ህልውና ዘመቻውን ለመደገፍ ስንቅ እያዘጋጁ ይገኛሉ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ÷ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በምስራቅ አማራ የጦር ግንባር እየተፋለሙ ላሉት የሰራዊት አባላት ያለ ድካም ስንቅ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

ድሉ የኛ ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ÷ ስንቅ ማዘጋጀት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ቀን ከሌት በህብረት ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን በመሆን እየተጋን ነውም ብለዋል።

ስራውን እየመራ የሚገኘው የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለምነው መልካሙ ÷ ዩኒቨርሲቲው ለህልውና ዘመቻው ዘርፈብዙ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አንስተው ÷እስካሁን 250 ኩንታል ደረቅ ሬሽን ተዘጋጅቶ ወደ ግንባር መላኩን ነው የተናገሩት።

ስራው አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ÷ አሁንም 400 ኩንታል ስንቅ ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በሳምራዊት የስጋት

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.