Fana: At a Speed of Life!

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

ክፍለ ከተማው እስካሁን 157 ሚሊየን 365 ሺህ ብር ለመከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ ማድረጉን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ቆንጅት ደበላ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የደም ልገሳ ተካሂዷል። ዘማቾችም ተሸኝተዋል ።

የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀ ነራል ጥሩዬ አሰፌ ክፍለ ከተማው ለሀገር መከላከያ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.