Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የወባ መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የወባ መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የመጀመሪያውን የወባ መከላከያ ክትባት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል። አቶ ሳሙኤል በዚህ…

የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ "ማሽቃሮ" በዓል በቦንጋ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በዓሉ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የብሔሩ ተወላጆች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው…

የጋሞ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ዮ ማስቃላ” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋሞ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ "ዮ ማስቃላ" በዓል በአርባምንጭ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። ዮ ማስቃላ በዓል በብሔረሰቡ ዘንድ ዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን ያዘነን የሚያጽናና፣ የተጣላን የሚያስታርቅ፣ የተራራቀን የሚያቀራርብ ልዩ ትርጉም…

የመስቀል በዓል አከባበር ሰላምንና ፍቅርን የሚሰብክ ሊሆን ይገባል – ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

የመስቀል በዓል አከባበር ሰላምንና ፍቅርን የሚሰብክ ሊሆን ይገባል - ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል በዓል የሰላም በዓል በመሆኑ የበዓሉ አከባበር ሰላምንና ፍቅርን የሚሰብክ ሊሆን ይገባል አሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን…

በሕዳሴ ግድብ ያሳየነውን የመቻልና መፈፀም አቅም በሌሎች የልማት ዘርፎችም እንደግማለን – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሳየነውን የመቻልና የመፈፀም አቅም በሌሎች የልማት ዘርፎችም እንደግማለን አሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ። የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ሲደረግ የነበረው…

ሕዳሴ ግድብ የማንሰራራት ከፍታ መሸጋገሪያ ማማችን ነው – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቅ ለጀመርነው የማንሰራራት ከፍታ መሸጋገሪያ ማማችን ነው አሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)። "በሕብረት ችለናል" በሚል መሪ ሐሳብ ግድቡ በስኬት መጠናቀቅን…

ጠንካራ የስራ ባህልን ያዳበረ ትውልድ መገንባት ያስፈልጋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአንድ ሀገር እድገትና ብልፅግና እውን መሆን በቴክኒክና ሙያ ጠንካራ የስራ ባህልን ያዳበረ ትውልድ መገንባት ያስፈልጋል አሉ። ከንቲባ አዳነች ይህን ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ስራና ክህሎት…

የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሥስት ወራት በብርቱ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በዛሬው ዕለት በድምቀት ይካሄዳል። በውድድሩ ለፍጻሜ የበቁት ጴጥሮስ ማስረሻ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ እዮቤል ፀጋዬ እና ኤፍሬም ጌታቸው ብርቱ…

ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም የጀመረችውን እንቅስቃሴ እደግፋለው አለ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በቪየና ኦስትሪያ እየተካሄደ ካለው 69ኛው የIAEA መደበኛ ጉባኤ ጎን…

የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት በማለም ለተጀመረው ርብርብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ። ዶ/ር ደረጄ የወባ መከላከያ ክትባትና የአልጋ አጎበር ስርጭትን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን…