Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ከንቲባ አዳነች ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመዲናዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተገነቡ ያሉ…

የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታትና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም- ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡   የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳይ…

ባለፉት ስምንት ወራት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት ሥምንት ወራት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው የግብር ትምህርት እና ኮሙኒኬሽን የሥራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ አግማስ ጫኔ እንዳሉት÷ ለመሰብሰብ የታቀደው ገቢ የክልሉን…

የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፉን ለማነቃቃት የሚረዳ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እየተሰጠ ነው – ዶክተር በለጠ ሞላ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲጂታል ኢኮኖሚ  ዘርፍን ለማነቃቃት የሚረዳ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እየተሰጠ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር ) ገለጹ፡፡ የአውትሶርሲንግ ማህበር ምስረታ ማብሰሪያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡…

ሁሉም በተሰማራበት መስክ ሀገርን ማስቀደም እንዳለበት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም በተሰማራበት መስክ ብሔራዊ ጥቅምን በማጠበቅ ሀገርን ሊያስቀድም እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡ መገናኛ ብዙኃን ለብሔራዊ ጥቅም በሚል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ አፈ ጉባኤ ታገሰ…

በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህታማማቾች 7ሺህ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ለገሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህታማማቾች በትውልድ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ያሰባሰቡትን 7ሺህ መጻሕፍት ለኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረክበዋል። ወ/ሮ አያንቱ አበበ በልጆቻቸው በኩል የተሰበሰቡትን መጻሕፍትን ለኤምባሲው አስረክበዋል።…

ኢትዮጵያ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም መርሕን ታከብራለች – አምባሳደር ጀማል በከር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮያ አምባሳደር ጀማል በከር ከሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴክሬታሪ አሳድ መጅድ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ሀገራቱ ያላቸውን የሁለትዮሽና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የኤምባሲው…

በጅማ ከተማ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ ለ2 ሺህ ሰዎች የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡ ስነስርዓቱ በቀርጫሼ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሁም በጅማ ከተማና ዞን አስተዳደር የተዘጋጀ ነው፡፡ በአፍጥር ስነ-ስርዓቱ የከተማው አቅመ ደካሞችን ጨምሮ…

ኢትዮጵያ ስደተኞችን በማስጠለል እየፈጸመች ላለችው በጎ ተግባር ድጋፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ወደ ግዛቷ ለሚመጡ ስደተኞች መጠለያ በመሆን እየፈጸመች ላለችው በጎ ተግባር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ገልጿል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የዓለም አቀፉ ፍልሰተኞች…

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በሶስት ሳምንታት ውስጥ 500 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዢ መፈጸም የሚያስችል ንቅናቄ ሊያካሂድ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 12ኛ አመትን ምክንያት በማድረግ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በሶስት ሳምንታት ውስጥ 500 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዢ መፈጸም የሚያስችል ንቅናቄ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል። ንቅናቄው “ወጣት ለህዳሴው እኔም ድርሻ…