Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ-19ን ለመከላከል በምንሰማቸው በጎ ውጤቶች ሳንዘናጋ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃችችን መቀጠል አለብን- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ለመከላከል በምንሰማቸው በጎ ውጤቶች ሳንዘናጋ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃችንን መቀጠል አለብን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት…

ለሸገር ዳቦ ፋብሪካ በኦን ላይን ስልጠና ብቁ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅርቡ ስራውን ለሚጀምረው ለሸገር ዳቦ ፋብሪካ በኦን ላይን ስልጠና ብቁ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉን ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከካቢኔ አባላት…

አየር መንገዱ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመጠለያ ውስጥ ለሚገኙ 400 ዜጎች ለ15 ቀናት የምሳ ምገባ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመጠለያ ውስጥ ለሚገኙ 400 ዜጎች ለ15 ቀናት የሚቆይ የምሳ ምገባ መርሃ ግብር አስጀመረ። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር…

በድሬዳዋ ከተማ በጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ በትናንትናው ዕለት የጣለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የአራት ሰዎች ህይዎት ማለፉን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ዝናቡ ትናንት ከቀኑ 7 ሰአት ከ30 ጀምሮ የጣለ ሲሆን፥ ያስከተለው ጎርፍ የመኖሪያ ቤቶችን…

በተወሰኑ የአሜሪካ ግዛቶች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ክፍት ሊሆኑ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተወሰኑ የአሜሪካ ግዛቶች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለአገልግሎት ክፍት ሊሆኑ ነው። ጆርጂያ፣ ኦክላሆማ እና አላስካ ግዛቶች የተወሰኑ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ፈቃድ ሰጥተዋል። ይህን ተከትሎም በጆርጂያ እና…

ከግለሰብ እስከ ሃገር ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሽያጭና ዝውውርን ለመከላከል ተባብረን ልንቆም ይገባል – ወይዘሮ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ላይ ከግለሰብ እስከ ሃገር ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሽያጭና ዝውውርን መከላከል እንደሚገባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አሳሰቡ። ጠቅላይ አቃቤ ህጓ ኢትዮጵያን ህገወጥ የጦር መሳሪያ…

በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የበረሃ አንበጣ መንጋ በበልግ ምርት ላይ የደቀነውን ስጋት ለመቀነስ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የበረሃ አንበጣ መንጋ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች መከሰቱን ተከትሎ የበልግ ምርት ላይ የደቀነውን ስጋት ለመቀነስ ስራ ተጀምሯል። በኦሮሚያ ክልል በተለይም በባሌ እና ቦረና ቆላማ አካባቢዎች አንበጣው በመከሰቱ የበልግ ምርት…

በኦጋዴን ተፋሰስ የለማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትን ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል ኦጋዴን ተፋሰስ የለማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትን ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል የተፈጥሮ ጋዝ የንግድ ስምምነት ተፈራረመ። በኦጋዴን አካባቢ 8 ትሪሊየን ጫማ የሚገመት የተፈጥሮ ጋዝና መጠኑ እየተለየ ያለ ፈሳሽ…

በኢትዮጵያ በቤት ለቤት ቅኝት ከ3 ሚሊየን በላይ ቤቶች ተዳርሰዋል – ዶክተር ሊያ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በተካሄደው የቤት ለቤት ቅኝት ከ3 ሚሊየን በላይ ቤቶች መዳረሳቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ሚኒስትሯ እንደገለፁት በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው የቅኝት ሥራ ዳሰሳው ተካሂዷል።…

የአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ገቢ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ማጠናቀቂያ ገቢ አደረጉ። የአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ…