Fana: At a Speed of Life!

ድምጻዊ አባይነህ ደጀኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሰርግ ሙዚቃን በሸክላ ያስቀረጹት አንጋፋው ድምጻዊ አባይነህ ደጀኔ ድንቁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አርቲስት አባይነህ ደጀኔ የሰርግ ሙዚቃ ሲነሳ ስማቸው አብሮ የሚነሳ ሲሆን÷ በተለይ በ1964 ዓ.ም በሆላንድ…

የሐዋሳ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ያለመከሰስ መብት ተነሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር ምርጫ 4ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ሦስት የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸውም÷ የሐዋሳ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ፣ አበራ አሬራ እና ተሰማ…

በሆልቲካልቸር ዘርፍ 741 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም በሆልቲካልቸር ዘርፍ 741 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የግብርና ሚኒስቴር በሆልቲካልቸር ዘርፍ ላይ ያሉ መልካም ዕድሎችና ተግዳሮቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው እንዲጫወት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን መስፈርቱን በማሟላት በሀገሩ ሜዳ ጨዋታውን እንዲያደርግ በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ገለጹ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 15ኛ መደበኛ…

ከ80 እስከ 90 በመቶ ያህሉ የሳይበር ጥቃት በተጠቃሚዎቹ ግንዛቤ ማነስ እንደሚከሰት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳይበር ደኅንነት ላይ ከሚደርሱ ጥቃቶች ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው በተጠቃሚዎቹ የግንዛቤ ማነስ የሚከሰት መሆኑ ተገለጸ፡፡ 3ኛ ሣምንቱን የያዘው 4ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ በአከባበሩ ላይ…

የሀገር ውስጥ ምርቶች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሊሠራ እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ ምርቶችን ጥራት በማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ተክተው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሊሠራ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡ የኢንዱሥትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርት ሥትራቴጅ ሠነድ ላይ ከዘርፉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላትና የአምራች…

በግብርና፣ ኢንዱሥትሪና ምኅንድስና ዘርፍ ለተሠማሩ የልማት ድርጅቶች ድጋፍ ይደረጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና፣ በኢንዱሥትሪ እና ምኅንድስና ዘርፍ ተሠማርተው ሃብት ለሚያመነጩ የልማት ድርጅቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የአማራ ክልል አስታወቀ፡፡ የአማራ ክልል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2016…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቤንቶኒቴ ማእድን ማውጫ እና ማምረቻን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፋር ክልል ዋርሰሶ ወረዳ የቤንቶኒቴ ማእድን ማውጫ እና ማምረቻን ጎብኝተዋል:: ቤንቶኒቴ ለሴራሚክ እና ቀለም ብሎም ለመሰል ምርቶች ጠቀሜታ በመዋሉ "ትንግርታዊ ርጥብ አፈር" እና "ብዝሃ ጥቅም…

ከ620 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን ላይን ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2016 ድረስ 621 ሺህ 437 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን ላይን መሠጠቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የላይሠንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ…

ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። አቶ ኦርዲን በአባድር ወረዳ ለሚገነባው ዘመናዊ ጤና ጣቢያ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት…