Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ የኢንቨስትመን ባንክ አገልግሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንቨስትመን ባንክ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል፡፡ ሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ማኅበር እና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አክሲዮን ማኅበር ደግሞ የመጀመሪያዎቹ…

ኢትዮጵያ እና ባርባዶስ በትብብር በሚሠሩበት ጉዳይ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በኬንያ የባርባዶስ ከፍተኛ ኮሚሽነር እና በናይሮቢ የተባበሩት መንግሥታት ቋሚ ተወካይ ከሆኑት ዊሊያም አሌክሳንደር ማክዶናልድ ጋር ተወያዩ፡፡ በዚሁ ወቅትም በትብብር መሥራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ…

5ኛው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት የሥራተደራዳሪ ቡድን ስብሰባ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አምሥተኛው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት የሥራ ቡድን ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ በተለያዩ የድርድር ነጥቦች ዙሪያ ከ110 በላይ ጥያቄዎችን በመቀበል ውጤታማ ድርድር…

ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ልምድ ለጋምቢያ አካፈለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በጋምቢያ የማዕከላዊ ባንክ ተቀዳሚ ምክትል ገዥ አብዱላዮ ሲረህ ጃሎ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡ በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ ከውኃ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት የዳበረ ልምድ…

ሀገራዊ የችግኞች የጽድቀት መጠን 85 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተከሉ ችግኞች የጽድቀት መጠን 85 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም አስታወቁ፡፡ የዓለም የደን ቀን በኢትዮጵያ መከበር መጀመሩን አስመልክቶ በተዘጋጀ ሁነት ላይ ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት፤…

አቶ ደስታ ሌዳሞ ለሕዝቡ የመሠረተ ልማት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ትኩረት መደረጉን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ለሕዝቡ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ። ርዕሰ መሥተዳድሩ፥ በክልሉ ምሥራቃዊ ሲዳማ ዞን በግንባታ ላይ ያሉ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን…

በውጭ ሀገር የተሰጠን ፍርድ በማስፈጸም 2 ነጥብ 25 ሚሊየን ዩሮ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በኔዘርላንድስ የሄግ ቋሚ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት ከ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ካሳ እንድትከፍል በቀረበባት ዓለም ዓቀፍ የኢንቨስትመንት ግልግል ዳኝነት ክስ ላይ ክርክር ተደርጎ ማስፈጸም መቻሉን የፍትሕ ሚኒስትር ወ/ሮ ሐና…

960 ተማሪዎችን የሚያስተናግደው አዳሪ ትምህርት ቤት በ243 ሚሊየን ብር ግንባታው እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአዳሪ ትምህርት ቤት ጎበኙ፡፡ ከ243 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ እየተገነባ ያለው ትምህርት ቤቱ፤ የመማሪያና የተማሪዎች…

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሺ ዲባባ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአጭር እና በረጅም ርቀት እንዲሁም ጥሩነሺ ዲባባ የታዳጊዎች እና የአዋቂዎችን ውድድር በአንድ ጊዜ በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል፡፡…

በስፋት እየተከሰቱ ያሉ ማጭበርበሮች በምን መልኩ ሊፈጸሙ ይችላሉ?

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ የማጭበርበር ወንጀሎች ቁጥራቸው ክፍ እያለ መጥቷል። ከማጭበርበር ጋር በተያያዘም ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርቶች ይቀርባሉ። በመሆኑም ግለሰቦች የሚፈጸሙ…