Fana: At a Speed of Life!

በቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት በተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከር የሚያግዙ ስምምነቶች ተደርገዋል – ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት ወቅት በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በንግድና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚያግዙ ስምምነቶች መደረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ በቬይትናም የተደረገውን ይፋዊ…

በባህር ዳር ከተማ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የሚካሄደው ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ዛሬ ተጀምሯል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት የተጀመረው ፕሮጀክቱ 800 ሜትር ርዝመትና 40 ሜትር ስፋት ያለው አስፋልት መንገድ…

ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆኗል። በጨረታ ሒደቱ 26 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን÷በዚህም የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ በአማካኝ 131 ነጥብ 4961 ብር ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡…

ወደ ግብር ከፋይ ሰንሰለት ያልገቡ አካላትን ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወደ ግብር ከፋይ ሰንሰለት ያልገቡ አካላትን ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገራዊ እና በገቢ ዘርፍ…

የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሻሻል ሚዲያዎች በኃላፊነት እንዲንቀሳቀሱ ያግዛል – ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሻሻል ሚዲያዎች በኃላፊነት እንዲንቀሳቀሱና ለሀገር ግንባታ የሚኖራቸውን ድርሻ ይበልጥ ከፍ እንዲያደርጉ የሚያግዝ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) ገለጹ። 6ኛው…

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ለተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት ተገቢውን ሚና ተወጥቷል – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በኢትዮጵያ ለተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ የአስቻይነት ሚናውን በሚገባ ተወጥቷል ሲሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ ገለጹ። ዓለሙ ስሜ (ዶር) እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተገኙበት…

ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሥርዓተ-ምግብ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅታ እየተገበረች እንደምትገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “ዘላቂ እና ህዝብን ማዕከል ያደረገ አረንጓዴ ሽግግር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው 2025 ፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ልምዷን አካፍላለች። በጉባኤው ከአረንጓዴ አብዮት ጋር የተጣጣመ ዘላቂ የሥርዓተ-ምግብ ሽግግር ላይ ያተኮረ…

በሱዳናውያን ባለቤትነት የሚመራ የሰላም ሂደት በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ ለመፍታት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ በሱዳን ጉዳይ በለንደን እየተካሄደ ባለው ጉባኤ እየተሳተፈ ይገኛል። በጉባኤው በሰብአዊ ዕርዳታ፣ የተኩስ አቁም ስምምነትን…

ከፍርድ ቤትና ከፖሊስ ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ስኬታማ አፈፃፀም ተመዝግቧል – የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፍትህ ዘርፍ ከፍርድ ቤትና የፖሊስ ተቋማት ጋር የተሻለ ቅንጅት በመፍጠር ስኬታማ አፈፃፀም መመዝገቡን የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያሥላሴ ገለጹ። ሚኒስትሯ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የፍትሕ ዘርፉን እንቅስቃሴ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፥ የወንጀል…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቬይትናም ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቬይትናም ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ጋር በፓርቲው ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም፤ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳዮች ብሎም በሀገራዊ ልማት እና አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡…