Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጥላሁን ከበደ በትምህርት ጉዳይ ሁሉም ባለድርሻ ተቀናጅቶ እንዲሰራ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) "በትምህርት ጉዳይ መምህራን፣ አመራር እና ወላጆች በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል” ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ፡፡ ‘የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራትና ለሀገር ብልፅግና’ በሚል መሪ ሃሳብ ክልላዊ የትምህርት ጉባኤ…

በሲዳማ ክልል ከ1 ሺህ 800 በላይ ተወካዮች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደሚሳተፉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ከ1 ሺህ 800 በላይ ተወካዮች በአጀንዳ አሰባሰብ የምክክር መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር መድረክ በነገው እለት በሲዳማ ክልል እንደሚጀምርም ገልጿል።…

በአማራ ክልል 806 ሺህ 476 ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016/17 የመኸር ምርት ወቅት 806 ሺህ 476 ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል መሸፈኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ በምርት ዘመኑ የስንዴ ምርታማነትን በሔክታር ወደ 41 ነጥብ 2 ኩንታል ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑንም ነው ቢሮው…

ሀብታችንን በአግባቡ ባለማስተዋወቃችን በወጪ ንግድ ማግኘት ያለብንን ጥቅም እያገኘን አይደለም – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገሪቱ ያላትን እምቅ ሀብት በአግባቡ ባለማስተዋወቃችን በወጪ ንግድ ዘርፍ ማግኘት ያለብንን ጥቅም እያገኘን አይደለም ሲሉ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ "የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ…

ዕዙ ያስመዘገባቸውን ድሎችና ያገኛቸውን ስኬቶች ከሕዝብ ጋር እያከበረ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት የምሥራቅ ዕዝ ባለፉት 47 ዓመታት ያስመዘገባቸውን አንጸባራቂ ድሎችና በተሳተፈባቸው ታላላቅ የልማት ሥራዎች ያገኛቸውን ስኬቶች ከሕዝብ ጋር በጋራ እያከበረ መሆኑን አስታወቀ። ዕዙ የተመሰረተበትን 47ኛ ዓመት በዓል…

 ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር የዓለም የጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ ልዑክ በአፍሪካ አህጉር የዓለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው። 74ኛው የአፍሪካ አህጉር የዓለም የጤና ድርጅት መድረክ የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሶ ንጉዌሶ በተገኙበት ዛሬ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ፍ/ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተጠርጣሪ ዮሃንስ ዳንኤል በርሄ…

በኮሪደር ልማት ሥራ የተመዘገበው ውጤት በተሻለ ፍጥነት ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በኮሪደር ልማት ሥራ የተመዘገቡ ውጤቶች በተሻለ ፍጥነት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ርብርብ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ። አቶ ኦርዲን በድሪ የሐረር ከተማን ስትራቴጂክ የልማት እቅድ ለመምራት ከተቋቋመው ግብረ…

ኢትዮጵያና ሞሮኮ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሞሮኮ ብሄራዊ መከላከያ አስተዳደር ተጠሪ አብዱላጢፍ ሉዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም÷ ሀገራቱ ያላቸውን ወታደራዊ ትብብር ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡…

በሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ23 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ23 ወገኖች ሕይወት ሲያልፍ ሥምንት ሰዎች የአካል ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ አደጋው የተከሰተው በዞኑ በሚገኙ አራት ወረዳዎች በሚገኙ 11 የገጠር ቀበሌዎች መሆኑን የዞኑ አደጋ…