Browsing Category
የሀገር ውስጥ ዜና
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን 4 ሴት ሕጻናት በደራሽ ውኃ ተወሰዱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ ከለኪንዶ ወንዝ አራት ሴት ሕጻናት በደራሽ ውኃ መወሰዳቸውን የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በውኃ የተወሰዱት ሕጻናት ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 15 እንደሚገመት የቡኢ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት…
1 ሺህ 178 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 178 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ መሆኑን…
በድሬዳዋ በተከሰተው የእሳት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ የገበያ ማዕከል ትናንት በተከሰተው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም በቅንጅት ርብርብ እንዲደረግ አቶ አደም ፋራህ ጥሪ አቀረቡ፡፡
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ወ/ሮ ሽዊት ሻንካ - የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር
2. ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር
3.…
በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ዐቃቤ ሕግ ምስክር አሰማ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር የምዝበራ ሙከራ ጋር ተያይዞ በተከሰሱት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክር አሰምቷል፡፡
የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ቃል የሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ…
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 381 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።
ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከልም 273ቱ ሴቶች ሲሆኑ 1 ሺ 108ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በ2ኛ…
ም/ቤቱ ነገ ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ…
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሃይሎች አብዛኛዎቹ ወደ ሰላም መምጣታቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ቡድኖች አብዛኛዎቹ ወደ ሰላም ፊታቸውን አዙረዋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳደሩ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ጋር ተወያይተዋል።…
በፕሪሚየር ሊጉ ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሃዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች አሊ ሱሌማን በ3ኛው እና 48ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
የሊጉ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲቀጥል ቀን 10 ሰዓት ላይ…
በመዲናዋ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 490 ጋላክሲ ሳምሰንግ ሞባይል ስልኮች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 490 ጋላክሲ ሳምሰንግ ሞባይል ስልኮች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ፖሊስ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ…