Browsing Category
የሀገር ውስጥ ዜና
ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን ጊዜ ቀጠሮ መዝገብን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል።
ቀሲስ በላይ ከአንድ ሳምንት በፊት በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ…
የብሪክስ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የጥናትና ምርምር ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን የብሪክስ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩም የብሪክስ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ በአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ፣…
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረት ስራ ኤጀንሲዎች ባዛርና ዓውደ ርዕይ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልል አቀፍ የህብረት ስራ ኤጀንሲዎች ባዛርና ዓውደ ርዕይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ተከፈተ።
የህብረት ስራ ማህበራት ለሁለንትናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ባዛርና ዓውደ ርዕዩ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም አምራች ህብረት ስራ…
የቻይናው ዘኒት ስቲል ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት አለኝ አለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ብረታብረቶችንና የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን አምራቹ ዘኒት ስቲል ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኩባንያው…
የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን የሚያደናቅፉ ችግሮችን ለመቅረፍ የጋራ ግንዛቤ መያዝ ይገባል- አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን የሚያደናቅፉ ችግሮችን ለመቅረፍ የጋራ ግንዛቤ መያዝ ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።
የምክር ቤቱ አባላት ከከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በሀገሪቱ አጠቃላይ…
የሥነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 52 አመራሮችና ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቀረቡ 95 ጥቆማዎች 36 አመራሮችና ሠራተኞች ጥፋተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ እርምጃ መወሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የቀሪዎቹ ጉዳይ ደግሞ በዲሲፕሊን ኮሚቴ በመታየት ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡…
በበጋ መስኖ ስንዴ ከ2 ሚሊየን ሔክታር በላይ ሰብል ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጋ መስኖ ስንዴ በዘር ከተሸፈነው 3 ሚሊየን ሔክታር ውስጥ 2 ነጥብ 1 ሚሊየኑ መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
እስካሁን ከተሰበሰበውም 73 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና…
በመዲናዋ በግንባታ ላይ ያለ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጊድ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግንባታ ላይ ያለ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አይዳ አወል…
የአፍሪካ ሀገራት ለቅድመ አደጋ መከላከል ስራ የተለየ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካ ሀገራት የቅድመ አደጋ መከላከል ላይ አበክረው በመስራት በአደጋ የሚመጣ ጉዳትን መቀነስ እንደሚኖርባቸው የአፍሪካ ሕብረት አሳሰበ።
14ኛው የአፍሪካ ሪስክ ካፓሲቲ ተቋም ስምምነት(ARC Treaty) ፈራሚ ሀገራት የሚኒስትሮች…
ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን መደገፍ ይገባል አሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን በጋራ መደገፍ ይገባል ሲሉ የመላው አፋር ህዝብ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ተናገሩ።
የእውቁ ሱልጣን አሊሚራህ ልጅ የሆኑት 15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ከውጭ…