Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ በክልሉ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ለሕግ በማቅረብ ጠንካራ አፈፃፀም መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገወጥ የሕፃናት ዝውውርን በመከታተልና ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ለሕግ በማቅረብ ጠንካራ አፈፃፀም መመዝገቡን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ከሕዝብና ከመንግሥት የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ከሚመለከታቸው…

በ“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ ሽያጭ በሚለማው የጢያ ዓለም አቀፍ መካነ-ቅርስ ዲዛይን ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥራ በሆነው “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ በሚለማው የጢያ ዓለም አቀፍ መካነ-ቅርስ ፕሮጀክት ዲዛይን ላይ በሆሳዕና ከተማ ምክክር ተደርጓል፡፡ በመድረኩም÷ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል…

ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጋቢት አጋማሽ እስከ ግንቦት መጨረሻ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ፡፡ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ለማ መሠለ…

የቲቢ በሽታን ለመግታት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቲቢ በሽታን ለመግታት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የዓለም የቲቢ ቀን በኢትዮጵያ ለ27ኛ ጊዜ "በእርግጥም የቲቢ በሸታ ሥርጭትን መግታት እንችላለን” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች…

ኢትዮጵያ ጠንካራ ብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ከገነቡ ሀገራት አንዷ ሆነች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጠንካራ ብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ከገነቡ ስድስት የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ መንግሥት አስፈላጊውን በጀት መድቦ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማትን መገንባት መቻሉ እና…

የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት መቀጠል አለበት – ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችን የአመራርነትና የውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ፡፡ በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት፣ ዩ ኤን ውሜን እና ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውዴሽን አስተባባሪነት ከሁሉም…

የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ወገኖች ላይ መሥራት እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁላችንም በምንችለው ሁሉ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ወገኖች ልንሠራ ይገባል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ፡፡ ዓለም አቀፉ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ቀን እና "መጋቢትን ከዲቦራ ጋር" መርሐ-ግብር በወዳጅነት…

በአፋር ክልል ያለውን ሀብት አልምቶ በመጠቀም ረገድ የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የሚገኘውን ሀብት አልምቶ በመጠቀም ረገድ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። በአቶ መላኩ አለበል የተመራ የፌዴራል ልዑክ በአፋር ክልል ሲያደርግ የቆየው ድጋፋዊ ጉብኝት…

የተለያዩ ሚኒስትሮች በክልሎች ሲያካሂዱት ለቆዩት ጉብኝት ግብረ መልስ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል የድጋፍና ክትትል ቡድኖች በተለያዩ ክልሎች በተከታታይ ቀናት ሲያካሂዱ የቆዩትን ጉብኝት አጠናቅቀዋል፡፡ የፌዴራል የድጋፍና ክትትል ቡድን ባለፉት 10 ቀናት በአማራ ክልል ሦስት ማዕከላት ያካሄደውን ድጋፋዊ ጉብኝት አስመልክቶ በባህርዳር…