Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ለ ‘አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ የተመደበው በጀት ለግል ጥቅም በመዋሉ ፓርቲው ታግዶ ምርመራ እንዲካሄድ ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም ለ‘አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ በምርጫ ቦርድ የተደረገለት የበጀት ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ ሳይውል ለግል ጥቅም መዋሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው የበጀት ድጋፉን ለታለመለት ዓላማ እንዳላዋለ እና…

ሀገር አቀፍ የፖሊስ ገለልተኛ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም የተቋቋመው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በስብሰባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል÷ የገለልተኛ ምክር ቤቱን ስራ የሚመሩ…

የጤና ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት ችግር ፈቺ መሆን እንዳለበት ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ተቋማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን የሚሰጡት አገልግሎት የህዝብን የጤና ችግር ፈቺ መሆን እንዳለበት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ገልፀዋል። የጤና ሚኒስቴር እና የክልል ጤና ተቋማት ተቆጣጣሪ አካላት የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ…

የኢትዮጵያና ፓኪስታን ሁለንተናዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ፓኪስታን መካከል ያለው ሁለንተናዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሸሪፍ ጋር በሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ…

ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ በቱሪዝም ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በቼክ ሪፐብሊክ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ መካከል እየተጠናከረ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በቱሪዝም ዘርፍም ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡…

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች እና ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተጉዘው ከተገኙ አባቶች ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤…

ሶስት ሀገር በቀል ኩባንያዎች የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት ፈቃድ አገኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስት ሀገር በቀል ኩባንያዎች መልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ፈቃድ አገኙ። ድርጅቶቹ የብቃት ማረጋገጫ እውቅና የምስክር ወረቀት ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እጅ ተቀብለዋል።…

በአዲስ አስተሳሰብና እሳቤ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የተረጋጋና ውጤታማ ጊዜያትን አሳልፈናል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አስተሳሰብና እሳቤ ጸጋዎቻችንን ከመለየት እስከ ሀብት መፍጠር ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የተረጋጋና ውጤታማ ጊዜያትን አሳልፈናል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት…

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች ለአቶ ደመቀ መኮንን የክብር ሽኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች ለቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ምስጋና እና የክብር ሽኝት አደረጉላቸው፡፡ አቶ ደመቀ በነበራቸው የአመራርነት ዘመን ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ነው…

2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016/17 ዓ.ም የምርት ዘመን 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ከክረምት በፊት ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በብሔራዊ የአፈር ማዳበሪያ ቴክኒካል ኮሚቴ ሥር…