Browsing Category
የሀገር ውስጥ ዜና
የሩዋንዳውያን የዘር ፍጅት 29ኛ አመት መታሳቢያ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁቱ እና ቱተሲ ጎሳዎች እርስ በእርስ የተገዳደሉበት የሩዋንዳው የዘር ፍጅት 29ኛ አመት መታሳቢያ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
በመታሰቢያ ስነ ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ÷ አንድ…
በመዲናዋ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የረመዳን ጾምን አስመልክቶ ነገ በአዲስ አበባ የሚደረገው የጎዳና ላይ ኢፍጣር በሰላም እንዲካሄድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁ አስታውቋል፡፡
"ኢፍጣራችን ለወገናችን" በሚል መሪ ቃል ነገ ቅዳሜ መጋቢት 30…
በግብርና ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ስራዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና ሌሎች…
የአቶ ሽመልስ አብዲሳን ስም በመጠቀም ህገወጥ የሲሚንቶ አከፋፋይ ማህበር በማደራጀት የተከሰሱ ግለሰቦች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጡ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ስም በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና ህገወጥ የሲሚንቶ አከፋፋይ ማህበር በማደራጀት ከ29 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ ስምንት ተከሳሾች እስከ 20 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና…
የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርናውን ዘርፍ በማሸጋጋር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢኮኖሚውን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና እንዳለው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተቀናጀ ግብርና ኢንዱስትሪ…
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።…
የአማራ ክልል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚተዳደሩበት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚተዳደሩበት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በተሰጠው ስልጣን መሰረት ክልሎች ከሚጠቀሙባቸው አዋጆች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ አዋጆችን እንዲያወጡና…
ከ47 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኮትሮባንድ ዕቃ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን 47 ሚሊየን 537 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ዕቃዎች ተያዙ፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ እንደገለጹት÷ መነሻውን ከጅቡቲ አድርጎ…
ለ2015/2016 የምርት ዘመን ከ15 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለማሰራጨት ዝግጅት ተደርጓል
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2015/2016 የምርት ዘመን ከ15 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለማሰራጨት ዝግጅት መደረጉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ…
በመዲናዋ በሕገ ወጥ የእህል ምርት አቅራቢዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በሕገ ወጥ የእህል ምርት አቅራቢዎች የሚደረጉ ግብይቶች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡
ከሕገ ወጥ አካላት ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግብይት ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ቢሮው ከፊታችን ሰኞ…