Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነት የሚያጸና በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለተግባራዊነቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ አባልና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር…

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡   በውይይቱ ላይ የሁለቱ ምክር ቤት አፈጉባኤዎች፣ ርዕሰ መስተዳድሮች እና…

8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት 8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀምሯል። በንግድ ትርዒቱ የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የአልባሣት፣ የቤት ማሥዋቢያ፣የቴክኖሎጂ እንዲሁም ኢንዱስትሪ ምርቶችና ፈጠራዎች…

ከታች ከቀረበው በመንግስት እና በህወሓት በኩል ከተፈረመው የሠላም ስምምነት ውጪ የተሰራጩ መረጃዎች ያልተሟሉና ሊያሳስቱ የሚችሉ ናቸው – አምባሳደር…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በመንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን ትክክለኛ ስምምነት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ÷…

በሦስት ክልሎች ሰላምና ልማት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የተዘጋጀ የሰላም ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ሰላምና ልማት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት የተዘጋጀው የሰላም ጉባኤ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው። በሐይማኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረው የሰላም ጉባኤ÷ የሕዝብ ለሕዝብ…

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላትጋር እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በተሣታፊዎች መለያ ረቂቅ እና አጀንዳ በማሠባሰብ አሠራር እና ሥርዓት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በደሴ ከተማ ውይይት እያደረገ ነው፡፡ በቆይታው ስለ ሀገራዊ ምክክሩ ፅንሰ-ሐሣብ ፣ስለ ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅና…

በውሃና ኢነርጂ ጉዳዮች ላይ ከኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃና ኢነርጂ ጉዳዮች ላይ ከኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት በሚያስችለው ጉዳይ ላይ ተወያይቷል፡፡ ውይይቱን ያካሄዱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ እና የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ዋና…

በኢንዱስትሪ ለውጥ እና በኢኮኖሚ ብዝሃነት ላይ ያጋራ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት በኢንዱስትሪ ለውጥ እና በኢኮኖሚ ብዝሃነት ላይ በኒጀር ኒያሚ ያጋራ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡ ምክክሩ በፈረንጆቹ ህዳር 20 ቀን 2022 የሚካሄደውን የአፍሪካን ኢንደስትሪያላይዜሽን እና የኢኮኖሚ ብዝሃነት…

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ኅብረት ጉባዔ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ኅብረት የጋራ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡ በጋራ ጉባዔው ላይ÷ የአባል ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች፣ ቻንስለሮች ችና የልቀት የምርምር…

የኢትዮ-ሳዑዲ አረቢያ ቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ ቢዝነስ ፎረም በበይነ መረብ ተካሂዷል። በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ የኤዥያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ዶ/ር ገበየሁ ጋንጋ ፥ የኢትዮጵያና የሳውዲ አረቢያ መንግስት በልማት…