Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ። የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ…

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 7 ተከሳሾች በሙስና ወንጀል ጥፍተኛ ተባሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጫላ ዋታን (ዶ/ር) ጨምሮ ሰባት ተከሳሾች በቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፍተኛ ተባሉ። ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተከሳሾች በቀረበባቸው ሁለት ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፍተኛ የተባሉ ሲሆን÷ 7ኛ ተከሳሽ…

ፕሬዚዳንት ታዬ በናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሬ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ። ፕሬዚዳንት ታዬ በጽሑፍ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ÷ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ናሚቢያን “መካከለኛ ገቢ ወዳለው ሀገር ያሻገሩ…

ህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀርቧል። በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ከህንድ የንግድ ተቋማት ሥራ ሃላፊዎች እና ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ውቅት አምባሳደር ፍስሃ÷ ኢትዮጵያ…

የአጀንዳ ባልተሰባሰበባቸው አካባቢዎች አስቻይ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ የህዝቡ ሚና ወሳኝ ነው – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ግጭት በሚታይባቸው አካባቢዎች ለምክክር ሂደቱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የህዝቡ ሚና ወሳኝ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ገልጸዋል፡፡ ዋና ኮሚሽነሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ‘አንድ ጉዳይ’ ጋር ባደረጉት…

የኢትዮጵያና ብሪታኒያ ሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ምክክር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያና ብሪታኒያ የሁለትዮሽ እና ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ እና ብሪታኒያ በፈተናዎች…

የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት አፈፃፀም 48 ነጥብ 5 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክትን እስከ ሐምሌ ወር ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ቴዎድሮስ ጋሻው እንዳሉት÷ ጣቢያው 14 ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጭ…

ቶዮ ሶላር በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ60 ሚሊየን ዶላር የተለያዩ ሶላር ፓኔሎችን ለማምረት የገባው የጃፓኑ ቶዮ ሶላር ኩባንያ የማሽን ተከላ ሥራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ…

የብሪክስ ሼርፓስ ስብሰባ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብራዚል ብራዚሊያ በተካሄደው የ2025 የመጀመሪያው የብሪክስ ሼርፓስ ስብሰባ ተጠናቅቋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በስብሰባው መካፈሉ ይታወቃል፡፡ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ብራዚል…

ለሽብር ተግባር መሰናዳት በሚል ክስ የቀረበባቸው ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሽብር ወንጀል መሰናዳት የወንጀል ክስ የቀረበባቸው 13 ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ፡፡ የግራ ቀኝ ማስረጃ መርምሮና አመዛዝኖ በ13 ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ፤ የሕገ መንግሥትና በሕገ መንግሥት…