Browsing Category
ስፓርት
ዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከታንዛኒያ ጋር ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመርያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ታንዛኒያን ይገጥማል፡፡
ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።
ዋልያዎቹ ትናንት በቤንጃሚን ምካፓ ናሽናል…
ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በአንደኛነት ያጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአፍሪካ በአንደኛነት ያጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካፈለው የኢትዮጵያ…
ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ 3 ሜዳሊያዎች በማግኘት ተሳትፎዋን አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው 17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያ 2 የወርቅና 1 የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ተሳትፎዋን አጠናቅቃለች።
በዚሁ መሠረት አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የጭላንጭል (T-13) እና ያየሽ ጌቴ በ1…
አትሌት ይታያል ስለሺ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ይታያል ስለሺ በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች በ1 ሺህ 500 ወንዶች አይነ ስውር ጭላንጭል (T-11) ፍጻሜ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።
አትሌቱ ርቀቱን 4 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃ…
ሱዋሬዝ ከመጪው ቅዳሜ ጨዋታ በኋላ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን እንደሚያገል አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዑራጋዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሉዊስ ሱዋሬዝ የፊታችን ቅዳሜ ከሚያደርገው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በኋላ ለሀገሩ እንደማይጫወት አስታውቋል፡፡
የ37 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ሀገሩ በመጪው ቅዳሜ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከፓራጓይ ጋር የምታደረገው ጨዋታ…
አትሌት ያየሽ ጌቴ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች አትሌት ያየሽ ጌቴ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የዓይነ ስውር (T-11) ፍጻሜ ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈች፡፡
አትሌቷ ቀደም ሲል 4 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ ከ68 ማይክሮ ሰከንድ በራሷ ተይዞ…
ሞሐመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር ሊለያይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ በ2024/2025 የውድድር ዓመት መጨረሻ ከክለቡ ጋር ሊለያይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል፡፡
ትናንት ሊቨርፑል በታሪካዊ ተቀናቃኙ ማንቼስተር ዩናይትድ ላይ ከተጎናጸፈው ድል በኋላ ለስካይ…
ሊቨርፑል ማንቼስተር ዩናይትድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 12ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ሊቨርፑል በሉዊስ ዲያዝ ሁለት ግቦችና በሞ ሳላህ አንድ ግብ ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስል ሲያሸንፍ ቸልሲ አቻ ወጥቷል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ኒውካስል ዩናይትድ ሲያሸንፍ ቸልሲ አቻ ወጥቷል፡፡
ቀን 9፡30 ኒውካስል ዩናይትድ ከቶተንሃም ባደረጉት ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የኒውካስልን ግቦች ሃርቤ ባርነስ እና…
በፕሪሚየር ሊጉ የላንክሻዬር ደርቢ በኦልድትራፎርድ ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት የላንክሻዬር ደርቢ ጨዋታ ዛሬ 12 ሠዓት ላይ ይደረጋል፡፡
ቀደም ሲል ከተደረጉ ሥድስት የላንክሻዬር ደርቢ ጨዋታዎች ሊቨርፑል አምስቱን እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድ አንድ ጊዜ…