Browsing Category
ስፓርት
ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ጎል አማኑኤል አድማሱ በጨዋታ ሲያስቆጥር የመቻልን ጎል ደግሞ ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡
በ41 ዓመቱ ፈጣኑን የማራቶን ሠዓት ያስመዘገበው አትሌት – ቀነኒሳ በቀለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት በማስመዝገቡ አድናቆት ተችሮታል፡፡
አትሌት ቀነኒሳ የዛሬውን የለንደን ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15…
አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 ማራቶንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 የማራቶን ውድድርን 2 ሠዓት ከ6 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት በበላይነት አጠናቀቀ፡፡
በተመሳሳይ በለንደን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት…
ኬንያ በተካሄደ የ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡
ትላንት ማምሻውን በኬንያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር ጎልድ ውድድር በ5 ሺህ ሜትር አትሌት ማርታ አለማየው አሸንፋለች፡፡…
የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩ ከ10 ሺህ በላይ ግለሰቦች እንዲሁም ከ22 ክለቦች የተወጣጡ አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመርተው ለዓለም አቀፍ ክለቦች…
ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ዛሬ 1:00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ለወላይታ ድቻ የማሸነፊያዋን ጎል ዘላለም አባተ በ80ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።…
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በነገው የለንደን ማራቶን ላይ ይወዳደራሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለማችን ታዋቂ አትሌቶች የሚሳተፉበት የ2024 የለንደን ማራቶን በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡
በውድድሩ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን÷ በወንዶች አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ሞስነት ገረመውና ታምራት ቶላ የአሸናፊነት ግምት…
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1 ሺህ 500 ሜትር በታሪክ ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1 ሺህ 500 ሜትር ርቀት በታሪክ ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈች።
በቻይና ዝያሜን እየተካሄደ ባለው ዲያመንድ ሊግ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50.30 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀች ሲሆን፤…
አትሌት ለሜቻ ግርማ በቻይና በተካሄደ 5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በቻይና ዢያሜን በተካሄደ የዲያመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈ።
12:58.96 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው አትሌት ለሜቻ ግርማ፤ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል በርካታ ድል በማስመዝገብ…
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ ሀምበሪቾን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ቀን 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማን ለድል ያበቃውን ጎል የሀምበሪቾው ዲንክ ኪያር በራሱ ላይ አስቆጥሯል።…