Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያና ዩክሬን በኒውክሌር ጣቢያ ላይ በተነሳው የእሳት አደጋ ተወነጃጀሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን እና ሩሲያ በግዙፉ ዛፖሪዝዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ምክንያት እርስ በርስ መወነጃጀላቸው ተሰምቷል። የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ እንደተናገሩት፥ በሩሲያ ከሁለት ዓመት በላይ ሲተዳደር የነበረው…

በኡጋንዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ የ21 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ እስከ አሁን የ21 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። በከተማዋ ኪቲዚ በተሰኘው የቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ነዋሪዎች በተኙበት የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ፥ በሰዎች፣…

የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ ግዛት ውስጥ እየተዋጉ መሆኑን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ ግዛት ዘልቀው በመግባት እየተዋጉ መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ገለጹ፡፡ ዘሌንስኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደራቸው በሩሲያ ምዕራባዊ ኩርስክ ግዛት ድንበር ውጊያ ላይ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን ፥ ጥቃት እያደረሰ…

በብራዚል በአውሮፕላን አደጋ የ62 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል ሳኦ ፖሎ ግዛት 58 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ በህይወት የተረፈ ሰው አለመኖሩ ተገለጸ። ባለ መንታ ሞተር ቱርቦፕሮፕ አውሮፕላን በደቡብ ብራዚል ፓራና ከምትገኘው ካስካቬል ወደ ሳኦ ፖሎ…

በጀርመን በወንዝ ዳርቻ የሚገኝ ሆቴል በከፊል በመደርመሱ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ሞስሌ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝ አንድ ሆቴል በከፊል በመደርመሱ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ጥቂቶች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል፡፡ ስምንት ሰዎች ደግሞ መውጫ አጥተው በወደቀው የህንፃ ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ የአካባቢው ፖሊስ…

ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈፀሙን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ ወደ ሰሜናዊ እስራኤል ተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሮኬት ጥቃቶችን መፈፀሙን ገለጸ፡፡ እስራኤል ባለፈው ሳምንት የቡድኑን ከፍተኛ አዛዥ መግደሏን ተከትሎ እየተጠበቀ ያለው የበቀል እርምጃ ገና ይቀጥላል ሲልም…

ሩሲያና ኢራን በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት ኢራን ቴህራን የገቡት የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሃፊ ሰርጌይ ሾይጉ በተለያዩ የሁለትዮሽ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከቴህራን ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ሾይጉ የእስላማዊ አብዮታዊ…

ፕሬዚዳንት ባይደን ኢራን በእስራዔል ላይ መዛቷን ተከትሎ ከብሔራዊ ደህንነት ቡድን ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን በእስራዔል ላይ ጥቃት ለማድረስ መዛቷን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሀገራቸው የደህንነት ቡድን ጋር መምከራቸው ተሰምቷል፡፡ በኢራን የሐማስ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬ እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ ቁልፍ አዛዥ መገደላቸውን ተከትሎ…

ብሊንከን ኢራንና ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢራንና ሂዝቦላህ በሚቀጥሉት 24 እና 48 ሰዓታት ውስጥ በእስራኤል ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣናዊ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት…

የእስራኤል ጦር በኢራን የሚፈጸምን ጥቃት ለመመከት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጦር ኢራን እፈጽመዋለሁ ላለችው ጥቃት አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በቅርቡ የሃማስ ከፍተኛ የፖለቲካ ሃላፊ ኢስማኤል ሃኒዬህ እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ ከፍተኛ አዛዥ በኢራን መገደላቸው…