‹‹እልፍ አእላፍ መከራዎች፣ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ሰው ሰራሽ ችግሮች ተደራርበው ያላስቆሙትን የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ራዕይን ተሸክመን ዛሬ ላይ ደርሰናል።
በደም የተከበረውን ሉዓላዊነታችንን በላብ ለማፅናት እያደረግን ያለነው ተጋድሎ በሕዝባችን ሁለንተናዊ ድጋፍ ውጤታማነቱ ቀጥሎ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና በሚያሻግሩ ስኬቶች ታጅበን ዛሬ ላይ መቆም ችለናል።
ኢትዮጵያ የሚያርፉባት የመከራ በትሮች ይበልጥ ፀንታ እንድትቆም አድርጓት፣ ሕዝቦቿ በፈተና መሀል…