Fana: At a Speed of Life!

ከዓለም ባንክ ከፍተኛ የስራ ሃለፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቢጀርድና ከዓለም ባንክ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ÷ በኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚና የልማት ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡…

የኢትዮ – ጃፓን የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ - ጃፓን የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ። ፎረሙ በኢትዮጵያ ያሉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው…

በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለው የባህር ሀይል መሰረታዊ ባህረኞች ማሰልጠኛ በዕቅዱ መሰረት ይጠናቀቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለው የባህር ሀይል መሰረታዊ ባህረኞች ማሰልጠኛ በዕቅዱ መሰረት እንደሚጠናቀቅ ተጠቆመ። በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ የተመራ ልዑክ በቢሾፍቱ እየተገነባ የሚገኘውን የባህር ሀይል መሰረታዊ…

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ከቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር በዱባይ ተገናኝተው ተወያይተዋለ፡፡ በውይይታቸው በሱዳን ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ በሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው…

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ በላይ አዲስ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መቐለ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን ከ1 ሺህ በላይ የተፈጥሮና የማህበረሰብ ሳይንስ አዲስ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ከሰተ ለገሰ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ተቋሙ…

የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል የተመሰረተበት 88ኛ ዓመት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ዓየር ኃይል የተመሰረተበት 88ኛ ዓመት እየተከበረ ነው፡፡ የምሥረታ ዓመቱ እየተከበረ የሚገኘው ‘በመስዋዕትነት ሀገርን የዋጀ የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል’ በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡ ከምሥረታ በዓሉ አከባበር ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የመንግሥት…

የአምራች ዘርፉን ውጤታማነት ማጠናከር የሚያስችል የፖሊሲ ማሻሻያ ተደርጓል – የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምራች ዘርፉን ውጤታማነት ማጠናከር የሚያስችሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ጨምሮ ሌሎች ተጨባጭ ተግባራት መከናወናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት መርሐ-ግብር ዓመታዊ የልማት ጉባዔውን በአዲስ አበባ እያካሄደ…

የኢትዮጵያ ልማት የጎረቤት ሀገራትን አብሮ ማደግ ማዕከል ያደረገ ነው – ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር )

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት የአካባቢውን ሀገራት የልማትና የለውጥ ፍላጎት ማዕከል ያደረገ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሯ ከሲ ጂ ቲ ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት÷ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እያደገ…

ኢትዮ ቴሌኮም በኦሮሚያ ክልል አገልግሎቱን ለማዘመን የሚያስችል ሥምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲሁም ከሸገር ከተማ አሥተዳደር ጋር አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን የሚያስችል የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ። ሥምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ እና በምክትል…

ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ለዘላቂ የኃይል ተደራሽነት ዓለም አቀፍ ጥምረት ለመፍጠር ተተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ከኮፕ28 ጉባኤ ጎን ለጎን በዘላቂ የኃይል ተደራሽነት ዓለም አቀፍ ጥምረት ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተገለጸ፡፡   የመግባቢያ ስምምነቱ የኢፌዴሪ ውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ…