Fana: At a Speed of Life!

ከጤፍ ዱቄት ጋር ሰጋቱራ በመቀላቀል ለሕብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጤፍ ዱቄት ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮችንና የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ) በመቀላቀል ለሕብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ሕገ-ወጥ ተግባሩ ሲፈፀም የነበረው በመዲናዋ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ…

በአትላንታ ከንቲባ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲከንስ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዱስ አበባ ገብቷል። ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ…

ከንጹሐን ዜጎች ግድያ ጋር ተያይዞ የጋምቤላ ክልል የቀድሞ የፖሊስ እና የልዩ ኃይል አዛዦችን ጨምሮ በ15 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ተፈጽሟል ከተባለ የንጹሐን ዜጎች ግድያ ጋር ተያይዞ በተጠረጠሩ የጋምቤላ ክልል የቀድሞ የፖሊስ ኮሚሽነሮችና የልዩ ኃይል አዛዦችን ጨምሮ በ15 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡ ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ተቀብለው አነጋገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልዕክተኛውን ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን አስታውቀዋል።

በኢዝላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢዝላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋ ተመርቋል፡፡ ኤምባሲውን መርቀው የከፈቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂና ራቢኒ ካሃን ናቸው። በዚህ ወቅት አምባሳደር ምስጋኑ…

በመዲናዋ ሲሚንቶ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ያወጣውን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ በመተላለፍ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው መንግሥት ያወጣው የሲሚንቶ ማከፋፈያና የችርቻሮ ተመን ዋጋ እንዲከበር ተደጋጋሚ…

ኢትዮጵያ በስዋዚላንድ የአፍሪካና ዓረቡ ዓለም ም/ቤቶች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴሬሽን ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ዛህራ ሁመድ የተመራ ልዑክ በስዋዚላንድ ማንዚኒ ከተማ የአፍሪካና የዓረቡ ዓለም ም/ቤቶች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው። በጉባዔው ላይ የተለያዩ የአፍሪካና የዓረቡ ዓለም አፈ ጉባዔዎች፣ የተለያዩ ሀገራት…

አምስት የፌዴራል ተቋማት ስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምስት የፌደራል ተቋማት የተገነቡ የስማርት ኮሚኒኬሽን ክፍሎች እና ስርዓት ተመርቆ ስራ ጀመረ። በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተገነቡ ስማርት ክፍሎቹ ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙና ለቀላልና…

የእንስሳትና የዓሳ ሃብት ልማትን ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀም ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የእንስሳትና የዓሳ ሃብት ልማትን ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ። ''የሌማት ትሩፋትን በመተግበር የስነ-ምግብ ዋስትናን እናረጋግጣለን'' በሚል መሪ -ቃል …

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣት እየሰራች ነው – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣት እየሰራች መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የአፍሪካ የግብርና ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ…