Fana: At a Speed of Life!

ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በሚሉ አጭበርባሪ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በማለት ኅብረተሰቡን እያጭበረበሩ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ የብሔራዊ መረጃና…

ሀሰተኛ የተሽከርካሪ የብድር ውል ማስያዣ ሰነድ በማቅረብ የማታለል ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ የተሽከርካሪ የብድር ውል ማስያዣ ሰነድ በማቅረብ በተፈጸመ የማታለል ተግባር በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ላይ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል የተባሉ 5 ተከሳሶች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ። ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ብይን…

የወጋገን ባንክ 8 ተጨማሪ ቅርንጫፎች ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋገን ባንክ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው በቆዩት በመቀሌ እና ሽረ ዲስትሪክቶች በሚገኙ ተጨማሪ ስምንት ቅርንጫፎቹ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ በዚህም በመቀሌ ዲስትሪክት÷ በውቕሮ፣ አጉላዕ፣ ዓዲ ጉደም፣ ዓዲ ሹምድሑን እና ክልተ አውላዕሎ…

የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የሰብዓዊና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎች ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የሰብዓዊ እርዳታና የአደጋ ስጋት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎች ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር  ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው…

 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ማራቶን ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች እንደሚሳተፉ የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡ በወንዶች ምድብ ሌሊሳ ዴሲሳ፣ሹራ ቂጣታ፣ አንዳምላክ በልሁ ፣ አንዱዓለም በላይ እንዲሁም ሂርጳሳ ነጋሳ በውድድሩ ይካፈላሉ፡፡ በሴቶቹ ደግሞ…

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዋን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ ከሰባት ዓመታት በፊት ሰጥቷት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በዛሬው ዕለት አስረክቧል። ወሎ ዩኒቨርሲቲ አርቲስት ማሪቱ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ላበረከተችው አስተዋጽኦ በ2008 ዓ.ም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ…

ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር በሐዋሳ ከተማ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያ ዙር ሀገር አቀፍ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን እና ባዛር በሐዋሳ ከተማ ተከፍቷል። ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ…

ኤምባሲው 200 ኢትዮጵያውን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 200 ኢትዮጵያውን  ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ የኬንያን ድንበር አቋርጠው የገቡ  መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ስለሆነም በኬንያ…

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ከፈረንሳይና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እና ከጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ፥ ጥልቅ እና ፍሬያማ…

አሜሪካ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ማጠናከር ትፈልጋለች-ትሬሲ ጃኮብሰን

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ማጠናከር ትፈልጋለች ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ተናገሩ፡፡ ለስራ ጉብኝት ጅማ ከተማ የሚገኙት ትሬሲ ጃኮብሰን÷ በከተማዋ እና…