Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚውል 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርጋለች፡፡ ድጋፉ በተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አማካኝነት በድርቅ ለተጎዱ አራት  ክልሎች የሚሰራጭ መሆኑ…

አሜሪካ ሠላምና ብልጽግና በኢትዮጵያ ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከክልላዊ አስተዳደሮች ብሎም ከማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሀገሪቷ ሠላምና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚሰሩ ሥራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች፡፡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር…

በደሴ ከተማ ከ250 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ አስተዳደር ከ250 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የአስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ ለአገልግሎት የበቁት በደሴ ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር…

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ዓላማውን በማስተዋወቅ ሂደት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ትብብርና ተቀባይነት ማግኘቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዓላማውን በማስተዋወቅ ሂደት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ትብብርና ተቀባይነት ማግኘቱን የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ገለጹ። የምክክር ኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ÷ ኮሚሽኑ ዓላማዎቹንና ሥራዎቹን…

ሐምሌ 19 የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል የንግሥ በዓል በሰላም ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ ሐምሌ 19 የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል እና በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተከብሯል፡፡ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምርያ ሃላፊ ኮማንደር ናስር መሀመድ በቁልቢ ገብርኤል የተከበረውን የንግስ በዓል አስመልክተው እንደገለጹት…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥቅምት 20 ወደ ዙሪክ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ስዊዘርላንዷ የንግድ ከተማ ዙሪክ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ የፊታችን መስከረም 9 ቀን 2015 ወደ ዮርዳኖስ ዋና ከተማ አማን በረራ እንደሚጀምር በትናንትናው ዕለት…

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን ከ5 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን ከ5 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የብሔራዊ አረንጓዴ አሻራ መርሐግብር የቴክኒክ ኮሚቴ ገለጸ። በኢትዮጵያ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር “አሻራችን ለልጆቻችን”…

ቻይና የአፍሪካና የቻይና የሰላምና ደኅንነት ትብብር እንዲጠናከር ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና-አፍሪካ የሰላም እና ደኅንነት ትብብር እንዲጠናከር የቻይና መከላከያ ሚኒስትር ዌይ ፌንጌ ጥሪ አቅርበዋል። ሚኒስትሩ በቪዲዮ በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ የሚኒስትሮች ፎረም ስብሰባ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በጽሑፍ ያስተላለፉትን መልዕክት…

በአፋር ክልል ያለውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በክልሉ ያለውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ የውይይት መድረኩ በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን÷ የክልል፣…

ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ ሆና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት አበረታች ነው- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ፡፡ የግብርና ምጣኔ ሃብት ተመራማሪዎች ዶክተር ከተማ በቀለ እና ዶክተር ስሜነህ ቢሴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር…