በዓለም ዋንጫ ሳዑዲ አርጀንቲናን ማሸነፏን ተከትሎ የሀገሪቱ ንጉስ ነገ የደስታ መግለጫ ብሄራዊ በዓል እንዲሆን አወጁ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ነገ ረቡዕ የዕረፍት እና የደስታ መግለጫ ቀን ሆኖ እንዲከበር አውጀዋል፡፡
ዐዋጁ የተላለፈው÷ የሀገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ላይ ያስመዘገበውን ድል ተከትሎ ነው፡፡…