Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካን በወላይታ ሶዶ ከተማ መርቀው ከፈቱ፡፡ ፋብሪካው በወላይታ ሶዶ ከተማ የተገነባ ሲሆን፥ ከዳቦ በተጨማሪ 42 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም…

ኖርዌይ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖርዌይ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና የመልሶ መቋቋም ሂደት አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር እና በአፍሪካ ሕብረት የኖርዌይ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንሰን ተናገሩ፡፡ አምባሳደር ስቲያን…

በመንግስት ምስጢራዊ መረጃ ምደባና ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ሚስጢራዊ መረጃ ምደባና ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ እና የቴክኖሎጂ ዝግጁነት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። አዋጁ የመንግስት መረጃዎችን ለመምደብና በየወቅቱ ለመፈተሽ እንዲቻል እና ሚስጢራዊ መረጃዎች እንዲጠበቁ እንዲሁም እንዳይሰራጩ ለማስቻል…

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ እና የህወሓት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ ተገናኝተው ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ እና የህወሓት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ ለሁለተኛ ጊዜ ተገናኝተው ተወያዩ። አዛዦቹ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ መክረዋል። ውይይቱን የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ሌሎች የአፍሪካ…

ቻይና ባለሃብቶቿን በግብርና፣ በማዕድንና በሌሎች መስኮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደምታበረታታ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ባለሃብቶች በግብርና፣ በማዕድን ልማትና በሌሎች መስኮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደሚያበረታቱም በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛኦ ዚያን ገልጸዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በኢትዮጵያ ከቻይና…

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንና ዩኒቨርስቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እና የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ እንዲሁም የመንግስት ዩኒቨርሰቲዎችን በመወከል…

ሚኒስቴሩ በጸሐይ ሃይል የሚሰሩ 9 የመስኖ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለመስኖ ልማት ምቹ በሆኑ አካባቢዎች በፀሐይ ሃይል የሚሰሩ ዘጠኝ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ይፋ ማድረጉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቀ።   ሚኒስቴሩ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ የፕሮጀክቱን አጀማመር…

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለገጣፎ ለገዳዲን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኢስማኤል ኦሮ አጉሮ ሁለት ግብችን ሲያስቆጥር÷ ፍሪፖንግ ሜንሱ እና ቸርነት ጉግሳ ቀሪ ግቦችን አስቆጥረዋል። ኢስማኤል…

ከሳዑዲ ዓረቢያ 1 ሺህ 106 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 106 ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ከሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሒደት ተጠናክሮ መቀጠሉንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው…