Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም እየሰሩ መሆኑን የደቡብ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እየሰሩ መሆኑን የደቡብ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አስታወቁ። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ በጦርነቱ የተጎዱ…

በዓለም ዋንጫው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል የምትሳተፍበትን ጨምሮ አራት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚህም በምድብ ሁለት የተደለደሉት ዌልስ ከኢራን ቀትር 7 ሰዓት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን ÷ በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት እንግሊዝ ከአሜሪካ ምሽት 4 ሰዓት…

26ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)26ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ " ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሠላም" በሚል ርዕሰ እየተካሄደ ነው። የውይይት መድረኩ በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ መድረኩ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ…

አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ዛሬ በኒጀር ኒያሚ ተወያይተዋል። በአቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ''የአፍሪካ…

በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ፖርቹጋል ጋናን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ ጨዋታ የአምስተኛ ቀን ውሎ በምድብ ስምንት በተደረገ ጨዋታ ፖርቹጋል ጋናን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ የፖርቹጋልን የመጀመሪያ ግብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በፍጹም ቅጣት ምት በ65 ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡…

የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያን የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ በኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካን ሶንኪይ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም  በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ለማጠናከርና እና በቀጣይ በኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት…

ዶክተር ሊያ ከ60 በላይ የመድሃኒት ዓይነቶች የሚያመርተውን ሳንሼንግ ፋርማቲካል ፋብሪካ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘውን የሳንሼንግ ፋርማቲካል ፋብሪካ ጎበኙ፡፡ በጉብኝታቸውም÷ የሳንሼንግ ፋርማቲካል ፋብሪካ የሚያመረታቸው የመድሃኒት ምርቶች ከመጋዘን ጀምሮ እስከ…

ቢሮው የተለያዩ የመስሪያ ቦታዎችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተለያዩ የመስሪያ ቦታዎችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ አስተላልፏል፡፡ ቢሮው ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት አገልግሎት ያልሰጡ፣ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ እና ለተጠቃሚ ተላልፈው…

ቤቶች ኮርፖሬሽን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን ከ269 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ለማዘመን ስምምነት ፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሕንጻን ለማደስና ለማዘመን የሚያስችለውን ስምምነት ፈረመ፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት፥ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል እና የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና…

የአየር ንብረት ለውጥ ለአፍሪካ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ለችግሩ መፍትሔ ማፈላለግ ያስፈልጋል – አቶ ዑመር ሁሴን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ንብረት ለውጥ በተለይ ለአፍሪካ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ለችግሩ መፍትሔ ማፈላለግ እንደሚያስፈልግ የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን ገለጹ፡፡   ግብርና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ያለው የግብርና የ15 ዓመት የኢንሹራንስ…