Fana: At a Speed of Life!

ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ሕዳር ወር በሚዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ሕዳር ወር ላይ በሚዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ላይ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ በማህበራ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷…

በመጀመሪያው ዙር አሸናፊው ያልተለየበት የብራዚል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወደ 2ኛ ዙር ተሸጋግሯል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጀመሪያው ዙር አሸናፊው ያልተለየበት የብራዚል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወደ ሁለተኛ ዙር መሸጋገሩን የሀገሪቱ ምርጫ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ በብራዚል 11 ዕጩዎች የተሳተፉበት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡ በተካሄደው…

ኮሚሽኑ በህግ ማስከበር ዘመቻ ተልዕኮና በስራ አፈጻጸም የላቀ ተግባር ለፈጸሙ ሠራተኞቹ ዕውቅና እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሀገራዊና ተቋማዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡና የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮች፣ አባላትና ሰራተኞች ዕውቅና እየሰጠ ነው፡፡ በመርሐ ግብሩ ከፍተኛ የስትራቴጂክ አመራሮች፣ ልዩ የስፖርት ተሸላሚዎች፣ የክልል…

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈተናውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም ፈተናው በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ…

በበጀት ዓመቱ 220 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት ማቀዱን የጢስ ዓባይ 2 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጢስ ዓባይ 2 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ2015 በጀት ዓመት 220 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ማቀዱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ደጀኔ ጉታ ተናገሩ፡፡ ዕቅዱን ለማሳካትና የኦፕሬሽን ሥራውን አስተማማኝ ለማድረግ መደበኛና ድንገተኛ…

ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰባሰበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ ገንዘቡ የተሰበሰበው መንግሥት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ…

የኢስታንቡል ነጻ የንግድ ቀጠና ከድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ጋር ትስስር መፍጠር እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢስታንቡል ነጻ የንግድ ቀጠና ከድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ጋር በጋራ ለመሥራት እና ትስስር ለመፍጠር ያለውን ፍላጎት ገለፀ፡፡ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የተውጣጣ ልዑክ በቱርክ የሚገኘውን የኢስታንቡል ነጻ የንግድ ቀጠናን ጎብኝቷል፡፡…

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከሶማሊያ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ከሶማሊያ አቻው ጋር ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ በሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር በምድብ ሀ የተደለደለው የታዳጊዎች ብሔራዊ ቡድን 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ…

የሶማሌ ክልል 620 ተፈናቃይ ዜጎችን በዘላቂነት አቋቋመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግሥት ተጨማሪ 620 ተፈናቃይ ዜጎችን በዘላቂነት አቋቋመ። በዘላቂ የመፍትሄ ስትራቴጂ ፕሮጀክት አማካኝነት የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ በቆሎጂ የተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ ይገኙ የነበሩ ተፈናቃዮችን ነው በዘላቂነት ያቋቋመው።…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሴናተር ጂም ኢንሆፈን ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፈን ተቀብለው አነጋገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል "ሴናተር ጂም ኢንሆፈ ወደ ኢትዮጵያ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ" ብለዋል።