Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪ በግንባታ ላይ ያለውን የድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ ማዕከል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ እየተገነባ ያለውን የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ ማዕከል ጎበኙ፡፡ አቶ ኦርዲን እንደገለጹት÷ ማዕከሉ ለምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሁሉ አገልግሎት ይሰጣል፡፡…

በለንደን እና ጣልያን በተካሄዱ የተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን የማራቶን፣ በጣልያን የግማሽ ማራቶን እና የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሮችን ኢትዮጵያ በበላይነት አጠናቀቀች፡፡ በለንደን የተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር በአትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊነት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡…

ኢሬቻ የአንድነት አርማ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ ተከብሮ ተጠናቋል – አቶ ፍቃዱ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ የዕርቅ፣ የወንድማማችነት፣የሰላምና የአንድነት አርማ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ ተከብሮ መጠናቀቁን በበልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ፡፡ አቶ ፍቃዱ በሰጡት መግለጫ፥ የኢሬቻ በዓል አንድነትና ወንድማማችነት…

አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ከአሜሪካ ሴናተሮች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ታገሠ ጫፎ የአሜሪካ ሴናተሮችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ አቶ ታገሠ ጫፎ በአሜሪካ ሴናተር የወታደራዊ አገልግሎት ኮሜቴ ሊቀመንበር ሚስተር ጀምስ ኢንሆፍ ከተመራው ጆን ሞዝማን እና…

በአማራ ክልል ከሐምሌ እስከ መስከረም አጋማሽ 163 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 2015 ዓ አጋማሽ ድረስ ከ163 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸው ተገለጸ። ከመስከረም 15 በኋላ የሚከስተውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል ያለመ ውይይት የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና…

የኢሬቻ በዓል አስደናቂ በሆነ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እናመሰግናለን – ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል አስደናቂ በሆነ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ በክልሉ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናለሁ ሲሉ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡ የኢሬቻ በዓል በሰላም…

ሚኒስቴሩ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጓል፡፡ ድጋፉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ ለአባገዳዎች እና ለዞኑ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች…

የኢሬቻ በዓልን በምስጋና እያከበርን ነው – የበዓሉ ተሳታፊዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል የምስጋና ቀን በመሆኑ በምስጋና እያከበርን ነው ሲሉ በቢሾፍቱ ተገኝተው እያከበሩ እንደሚገኙ የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡ የዘንድሮ የሆረ ሀርሰዴ በዓል አባገዳዎች የኢሬፈና ስነስርዓት በማካሄድ በይፋ አስጀምረውታል፡፡ በመርሐ…

የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻን ለማክበር የበዓሉ ተሳታፊዎች በጉጉት እየጠበቁ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆረ ሀርሰዲ ኢሬቻን ለማክበር የተገኙ የበዓሉ ተሳታፊዎች ቀድመው በበዓሉ ማክበሪያ በመገኘት ጅማሬውን እየተጠባበቁ ነው። አዳራቸውን በከተማዋ ጎዳናዎች ህብረ ዝማሬዎችን ሲያሰሙ ያደሩ ወጣቶች አሁንም የምስጋና ዜማዎችን በማሰማት ላይ ናቸው።…

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ወግና ባህል ያላቸው ህዝቦች መገኛ ናት – አባገዳ ጎበና ሆላ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ወግና ባህል ያላቸው ህዝቦች መገኛ መሆኗን አባገዳ ጎበና ሆላ ተናገሩ፡፡ በቢሾፍቱ የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል መከበር ጀምሯል፡፡ በበዓሉ የተገኙት አባገዳ ጎበና ሆላ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ እኛ ኢትዮጵያውያን…