Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታግደዉ የነበሩ አገልግሎቶችን መስጠት ሊጀምር ነዉ

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀመሩ የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ ኤጅንሲዉ ከዚህ ቀደም በሃገር አቀፍ ደረጃ ከአዲስ የነዋሪነት መታወቂያ…

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት መልካም ዜና መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት መልካም ዜና መሆኑን በዘርፉ ስራ ላይ የተሰማራው የሰሜን ኢኮቱርስ መስራችና ባለቤት ማርኮ ዳጋስፐር ተናገረ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከስሎቪኒያ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ6ኛው የአውሮፓ ኅብረት - አፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በቤልጂየም ብራሰልስ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስሎቪኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት…

አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ቦዲቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሦስት ወንድ ልጆችን በሰላም ተገላገለች። የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ወልዴ ቡቃቶ፤ እናቲት በሆስፒታሉ በቂ የቅድመ ወልድ ህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩ…

በጌዴኦ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ አደጋው ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ 45 ሰው ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡ በዚህም የ6…

በኢፋድ ድጋፍ የሚካሄዱ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና አላቸው – አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት የግብርና ልማት ዓለም አቀፍ ፈንድ (ኢፋድ) ፕሮግራም የሚካሄዱ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አቶ ርስቱ ይርዳ ገለጹ። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ከግብርና…

በሀረሪ ክልል ድህነትን ለመቀነስና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ድህነትን ለመቀነስና እና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ። በክልሉ ሁለተኛው ዙር የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በይፋ የተጀመረ ሲሆን÷ በመድረኩ…

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ የራሱን “ድሮን” በመሥራት የተሳካ የሙከራ በረራ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሜካኒካል ምኅንድስና ምሩቅ የሆነው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አማኑኤል ባልቻ ድሮን በመሥራት የተሳካ የሙከራ በረራ ማድረጉ ተገለጸ፡፡ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ ÷ መምህሩ የሠራው ድሮን 250…

የሲዳማ ክልል በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ለኦሮሚያ ክልል በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል የ20 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ድጋፉን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ…