Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የሚስተዋለውን ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሀረሪ ክልል እየተከናወነ የሚገኘውን ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በክልሉ የተካሄዱ ህገ-ወጥ የቤት ግንባታዎችንና የመሬት ወረራ ለማስመለስ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል፡፡…

በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የመገጭ ግድብ ግንባታ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እየተገነባ ላለው የመገጭ ግድብ ግንባታ መጓተት ምክንያት የሆኑ ችግሮች ተፈተው የግባታ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ መቀጠሉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ስራ ተቋራጭነት በ2005 ዓ.ም ግንባታው…

ለ30 ዓመታት ፊቱ ከታፋው ጋር ተጣብቆ የቆየው ግለሰብ በተደረገለት ቀዶ ጥገና ቀጥ ብሎ መቆም ችሏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሶስት አስርት ዓመታት  ፊቱ  ከታፋው ጋር ተጣብቆ  የቆየው ግለሰብ  በተደረገለት የተሳካ ቀዶ ጥገና ህክምና ቀጥ ብሎ መቆም መቻሉ ብዙዎችን አስደስቷል። የ46 ዓመቱ ሊ ሁዌ ከ18 ዓመቱ  ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት ፊቱን  ከታፋው ጋር በማጣበቅ…

የኡበር ተባባሪ መስራች ትራቪስ ካላኒክ ከቦርድ አባልነታቸው ሊለቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012(ኤፍቢሲ) ኡበር የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ተባባሪ መስራች ትራቪስ ካላኒክ በዓመቱ መጨረሻ ከቦርድ  አባልነታቸው ሊለቁ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡ ይሁን እንጂ የ43 ዓመቱ ትራቪስ በድርጅቱ ውስጥ ካሉ ዘጠኙ ዳይሬክተሮች ውስጥ አንዱ ሆነው የሚቀጥሉ…

የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስትን ለማስጠገን የ400 ሚሊየን ብር ጥናት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንጻዎችን ለመጠገን የ400 ሚሊየን ብር የፕሮጀክት ጥናት መጠናቀቁን የጎንደር የዓለም አቀፍ ቅርሶች አስተዳዳሪ አስታወቁ። አስተዳዳሪው አቶ ጌታሁን ስዩም ለኢዜአ እንደገለፁት፥ የፕሮጀክት ጥናቱ በቀጣዮቹ አምስት…

ፌስቡክ አንድሮይድን የሚተካ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እያበለፀገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እያበለፀገ መሆኑን ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። ኩባንያው የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚሰራውም ከጎግል አንድርይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ከአይፎን አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያለውን ጥገኝነት…

ዶክተር አሚር አማን በሶማሌ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ከሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት አደረጉ። ጉብኝቱ በጎዴ፣ ሸበሌ ዞን እና ቀላፎ ወረዳ የተደረገ ነው። በጉብኝታቸውም በጎዴ ከተማ ሸበሌ ዞንና…

የቼልሲው ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገር የ11 ሴራሊዮናውያን ህፃናትን የቀዶ ጥገና ህክምና ወጪ ሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 11 ሴራሊዮናውያን ህፃናት በቼልሲው ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገር ወጪያቸው ተሸፍኖ የቀዶ ጥገና ህክምና ተደረገላቸው፡፡ በተጫዋቹ ወጪያቸው ተሸፍኖ የቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው ህፃናት የከንፈር መሰንጠቅ፣ በቃጠሎ የተጎዱ እና በሰውነት አካላቸው…

በገና በዓል በቱሪስቶች የምትጨናነቀው የቤተልሄም ከተማ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ቁጥር ያላቸው ቱሪስቶች እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን ለማክበር ወደ ቤተልሔም  ከተማ ያቀናሉ፡፡ በዛሬው ዕለትም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ተጓዦች እና ቱሪስቶች በእስራኤል እየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት…

በቡርኪናፋሶ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የ35 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የ35 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። ጥቃቱ  በሀገሪቱ አንድ ከተማ ላይ በሚገኝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ የተፈጸመ መሆኑን  የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። በታጣቂዎች በተፈጸመው በዚህ ጥቃት  …