ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ ሙሉ መልዕክት
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
የሰላም፣ የአንድነትና የብራ ንጋት መልካም ምኞት ምልክት የሆነው ኢሬቻ፤ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ ወጥቶ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ትልቅ በዓል ነው።
ዝናብ ሰጥቶ ያበቀለውን ፈጣሪ፣ የክረምቱን ጎርፍና በረዶ በሰላም አሳልፎት…