Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ትብብር ለኢትዮጵያ የልማት ሥራ ድጋፉን እንደሚቀጥል አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች የገንዘብ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ትብብር አስታውቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ትብብር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማክታሃር ዲዮፕ እና ከሁሉን አቀፍ…

እነ ቀሲስ በላይ መኮንን እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ በሐሰተኛ የክፍያ ሠነድ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያወጡ ሲሉ ተይዘዋል ተብለው በከባድ ማታለል ሙስና ወንጀል የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ፡፡ ዛሬ ብይኑን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ…

108 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል- ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 108 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለባለሃብቶች መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት 108 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ…

 የአየር ክልሌ ለሌሎች ሀገራት ጥቃት እንዲውል አልፈቅድም- ኢራቅ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራቅ “እስራኤል የአየር ክልሌን ጥሳ በኢራን ላይ ጥቃት ፈጽማለች” ስትል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ እና የፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ አቀረበች፡፡ የኢራቅ መንግሥት በጻፈው የእስራኤልን ድርጊት የሚኮንን ደብዳቤ÷ “እስራኤል…

125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ…

የኢትዮጵያና ቻይናን ጽኑ ወዳጅነት ለማስጠበቅ እንሠራለን- የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ለዓመታት የቀጠለውን ጽኑ ወዳጅነት ለማስጠበቅ እንደሚሠራ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አስታወቀ፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል…

በሲዳማ ክልል መሬት ወስደው ባላለሙ ከ30 በላይ ፕሮጀክቶች ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለንግድና ኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ ከ30 በላይ ፕሮጀክቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን የሲዳማ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ ወሰንየለህ ስምኦን በሰጡት መግለጫ÷ የክልሉ መንግሥት የንግድና ኢንቨስትመንት…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብና የምክክር ምዕራፍ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ምዕራፍ ሒደትን አስጀምሯል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)÷መሰረታዊ የሃሳብ ልዩነቶችና አለመግባባቶች እየሰፉ በመምጣታቸው…

አሜሪካ ለታይዋን የፈጸመችው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውል ቻይናን ክፉኛ አስቆጣ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለታይዋን የፈጸመችው የ2 ቢሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውል የቻይናን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የጣሰ ነው ስትል ቤጂንግ ከሰሰች፡፡ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ቻይና በአሜሪካና ታይዋን የተፈጸመውን የ2 ቢሊየን…

የብሔራዊ ባንክ የዋሽንግተን ቆይታ ስኬታማ ነው – አቶ ማሞ ምኅረቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ያደረገው ቆይታ ግቡን የመታና ስኬታማ መሆኑን የባንኩ ገዥ ማሞ ምኅረቱ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ያካተተ ከፍተኛ…