Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎችን የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አስታወቁ፡፡ የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ላይ…

በፊሊፒንስ በመሬት መንሸራተት የ81 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 25 ዜጎች የገቡበት አልታወቀም

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ምዕራብ ፊሊፒንስ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የ81 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ተጨማሪ 25 ዜጎች የገቡበት አለመታወቁ ተሰምቷል፡፡ አደጋው ባልተለመደ መልኩ ለ24 ሰዓት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ መከሰቱን የገለጹት የሀገሪቱ…

ካንሰርን ለመከላከል ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ካንሰርን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አስታወቁ፡፡ ዓለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውንዴሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት ዓመታዊ የጡት ካንሰር ወርን ምክንያት…

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቫሌንሺያ ሜዲዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረወሰንን በመስበር ጭምር አሸነፈ፡፡ አትሌቱ ርቀቱን ያጠናቀቀው 57 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት መሆኑን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡ የዓለም…

መድኃኒትን በሀገር ውስጥ ለማምረት የተጀመረው ሥራ አበረታች ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መድኃኒትን በሀገር ውስጥ ለማምረት የተጀመረው ሥራ አበረታች መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን የሚከናወነው የየም ብሔረሰብ ዓመታዊ ባሕላዊ መድኃኒት ለቀማ ‘ሳሞኤታ’ በፎፋ ወረዳ በቦር ተራራ የፌደራል እና የማዕከላዊ…

የኮምቦልቻ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች የሰላም የእግር ጉዞ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች የሰላም የእግር የእግር ጉዞ አድርገዋል፡፡ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሙሐመድ አሚን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ከተማዋ በሰላምና በልማት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡ ከልማት…

 በአዋሽ ፈንታሌ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ ቀበሌ ጎምዲሊ በተባለ ሥፍራ እስከ 4 ነጥብ 7 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ ትናንት ከማለዳው 11 ሠዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ…

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ቻይና ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ቻይና ቤጂንግ ገባ፡፡ ልዑኩ ቤጂንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በቻይና ኮሙኒስት…

በደንበኞቼ ሠነዶች ላይ ጉዳት አልደረሰም- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ሸማ ተራ በነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማኅበር ሕንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የደንበኞቹ ሠነዶችና መረጃዎች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አረጋገጠ፡፡ አደጋውን ተከትሎ ሸማ ተራ ቅርንጫፍ…

አርሰናል ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዛሬው የጨዋታ መርሐ-ግብር መሠረት÷ ክሪስታል ፓላስ ከቶተንሃም ሆትስፐር፣ ቼልስ ከኒውካስል እንዲሁም ዌስትሃም ከማንቼስተር ዩናይትድ በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡…