“መስከረም በበርካታ የሀገራችን አካባቢዎች ወርቃማ ባህሎቻችን፣ ትውፊቶቻችን፣ ወግ እና ዘይቤያችን ጎልተው የሚወጡበት ወር ነው።
በርካቶች እንደ ወግና ልማዳቸው ዘመን የሚቀይሩበት፣ ይቅር የሚባባሉበት፣ አፈሩን ቀድሶ ምድሩን አለስልሶ ሀገር ያስረከባቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ የተበደለ የሚካስበት ነው መስከረም።
የኦሮሞ ሕዝብ ትውፊታዊ መገለጫ እሬቻ፣ የወላይታ የዘመን መለወጫ ዮዮ ጊፋታ፣ የሀዲያ…