Fana: At a Speed of Life!

ታማሚ አሳፍሮ ወደ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተገልብጦ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዳሰነች ወረዳ ታማሚ አሳፍሮ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተገልብጦ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ አደጋው የደረሰው በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ አርጎ ቀበሌ…

በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በ183 ጣቢያዎች ፈተናው መሰጠት መጀመሩን የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡…

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ካሜሩን አቀና

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ወደ ካሜሩን ዱዋላ አቀና፡፡ 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በካሜሩን አስተናጋጅነት በዱዋላ እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ…

ቱርክ ጆርጂያን 3 ለ 1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሽት 1ሰዓት ላይ በተደረገ የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ 6 ጨዋታ ቱርክ ጆርጂያን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ የቱርክን የማሸነፊያ ጎሎች መርት ሙልደር ፣ አርዳ ጉለርና ሙሀመድ ከሪም አክቱር ኮግሉ ሲያስቆጥሩ ጆርገስ ሚካታድዝ…

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራት የጀስቲስ ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሚመራ ልዑክ ቡድን ሩሲያ በሚካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት የጀስቲስ ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ በሩሲያ ሶቺ ከተማ ትናንት መካሄድ የጀመረው ፎረሙ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቀጥል…

ም/ ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእምነበረድና የቀርከሃ ፋብሪካዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእምነበረድና የቀርከሃ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን፣ የማዕድን ሚኒስትር ሐብታሙ ተገኝ(ኢ/ር) ና ሌሎችም የመንግሥት…

ጤና ሚኒስቴር እና ግሎባል ፈንድ ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር እና ግሎባል ፈንድ የቲቪ፣ የኤች አይ ቪ እና የወባ በሽታዎችን መቆጣጠር የሚያስችል ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመዋል፡፡ ስምምነቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና በግሎባል ፈንድ የአፍሪካ ዲፓርትመንት…

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ። ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ መሆኑን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው…

የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ የመልሶ ማልማት ስራ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር አስችሏል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስን ህልውና ጠብቆ ለማቆየት የተሰራው የመልሶ ማልማት ስራ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር ማስቻሉን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ። አቶ ኦርዲን በጁገል ዓለም አቅፍ ቅርስ የመልሶ ማልማት…

የመከላከያ ሚኒስትሯ ከጣሊያን አምባሳደር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር) ከኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎሰቲኒ ፓሌዝ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ ታሪካዊ የሆነውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ትብብሮችን ለማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ…