Fana: At a Speed of Life!

በየቀኑ ለ365 ቀናት ከማራቶን በላይ ርቀት የሮጠችው ብርቱ ሴት

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓመቱን ሙሉ በየቀኑ ከማራቶን በላይ ርቀት ሮጣ በብቃት ያጠናቀቀችው ብርቱ ቤልጄማዊት ሂልዴ ዶሶኜ ዕድሜዋ 55 ነው፡፡ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ውስጥም የባዮ-ኢንጂነር ባለሙያ ሆና ታገለግላለች፡፡ በፈረንጆቹ 2024 የመጨረሻ ዕለት የመጨረሻ…

በመርካቶና አንዳንድ አካባቢዎች የደረሠኝ ቁጥጥሩ ውጤት አምጥቷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መርካቶን ጨምሮ በሥምንት ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ዋና ዋና የግብይት ሥፍራዎች ደረሠኝ በመቁረጥ እና ተያያዥ ጉዳይ ላይ እየተከናወነ ያለው ቁጥጥር ውጤት አምጥቷል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡ ከተማዋ ማግኘት…

አርሰናል ብሬንትፎርድን በሜዳው አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወደ ጌቴክ ኮሚኒቲ ስታዲየም ያቀኑት መድፈኞቹ ብሬንትፎርድን 3 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡ ምንም እንኳን ንቦቹ በብሪያን ሙቤሞ ግብ ሲመሩ ቢቆዩም÷ ጋብሬል ጀሱስ፣ ሚኬል ሜሪኖ እና ጋብሬል ማርቲኔሊ…

የጤና አገልግሎቱን ለማሳደግ የዳያስፖራው ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል የጤና አገልግሎትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አስገነዘቡ፡፡ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ለሱልጣን ሼክ ሀሰን የበሬ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ…

ወደ ሲዳማ ክልል የአፈር ማዳበሪያ መግባት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017/18 ምርት ዘመን የሚሆን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሲዳማ ክልል መግባት መጀመሩን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ለምርት ዘመኑ 171 ሺህ ዳፕ እና 129 ሺህ ዩሪያ በአጠቃላይ 300 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ…

ሠራዊቱ ከተልዕኮው ባሻገር ሰፋፊ የልማት ሥራ እያከናወነ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መከላከያ ሠራዊት ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመፈፀም ጎን ለጎን ሰፋፊ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።  ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመከላከያ ተቋማት የኮሪደር ልማት አካል የሆኑ…

ከባሕርዳር ወደ ላሊበላ የቀጥታ በረራ ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከባሕርዳር-ላሊበላ እና ከላሊበላ-ባሕርዳር የቀጥታ በረራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመላከተ፡፡ የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አበበ እምቢአለ ለፋና ዲጂታል…

ፕሬዚዳንት ታዬ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ለሚያከብሩ ሁሉ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ በዓለም ላይ የ2025 አዲስ ዓመትን ለሚያከብሩ ሁሉ÷ ዓመቱ የሰላም እና የብልጽግና እንዲሆላቸው በማኅበራዊ…

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የፓውዛና ስክሪን ገጠማ በቅርቡ እንደሚከናወን ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በቅርቡ የምሽት ጨዋታዎች ለማካሄድ የሚያስችሉ የፓውዛ መብራት፣ የጃይንት ስክሪን፣ የክብር እንግዶች የሚቀመጡበት ወንበር ገጠማ እንደሚከናወንለት ተገለጸ፡፡ አጠቃላይ የስታዲየሙ ግንባታ አፈጻጸም 82 ነጥብ 47…

በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ ያቀረቡ 31 አርሶ አደሮች ተፈቀደላቸው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 31 አርሶ አደሮች እንዲያለሙ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አሥተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡ ከከተማው ዕድገት አብረው ማደግ ሲገባቸው ከልማቱ ሲገፉ የነበሩ በከተማው ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮችን…