ስፓርት
አትሌት ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃማይካ እየተካሄደ በሚገኘው ግራንድ ስላም ትራክ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አሸንፋለች።
አትሌት ድርቤ ርቀቱን 4:04.51 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች።
አትሌቷ በ800 ሜትር 2ኛ የወጣችበት ውጤት ተደምሮ በአጠቃላይ ያገኘችውን ነጥብ 20 ማድረሷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።
Read More...
ባለ ንስር ዐይኑ ጎል ቀማሚ – ኬ ዲ ቢ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቁጥሮች አይዋሹም ይባላል፤ በዘጠኝ ዓመት የውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት ቆይታው ከሪያን ጊግስ ቀጥሎ በፕሪሚየር ሊጉ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ስሙን በስኬት መዝገብ አስፍሯል።
ጎል ከማይነጥፍበት የማንቸስተር ሲቲ የፊት መስመር ጀርባ በንስር ዐይኑ አሻግሮ በማማተር ኳስን ሲጠበብባት ዓለም የተመለከተው ኮከብ ከቁጥሮችም…
ኬቨን ዲብሮይን በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ተረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቤልጂየማዊው የማንቼስተር ሲቲ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዲብሮይን ከዘጠኝ ዓመት ቆይታ በኋላ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከቡድኑ ጋር እንደሚለያይ ተረጋግጧል፡፡
ተጫዋቹ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የሚጠናቀቅ በመሆኑ በነፃ ዝውውር ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በክለቡ…
በእግር ኳስ ህይወቱ ቀይ ካርድ ያለተመለከተው ኢኔሽታ …
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ላማስያ አካዳሚ በመነሳት እልፍ አእላፍ ስኬቶችን የተጎናፀፉ አሉ።
እንደእነ ሊዮኔል ሜሲ፣ ዣቪ ሄርናንዴዝ እና ሰርጂዮ ቡስኬት የመሳሰሉ ተጨዋቾች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።
ስፔናዊው የባርሴሎና የቀድሞ የመሀል ሜዳ ተጫዋች አንድሬስ ኢኔሽታም ከዋነኞቹ አንዱ ነው።
በተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ጭምር…
ኢትዮጵያ መድን ሀዋሳ ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ መሪነቱን ማጠናከር ችሏል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ አበራና አቡበከር ሳኒ ሲያስቆጥሩ ÷የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ ቸርነት አውሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡…
ፋሲል ከነማ ወልዋሎ ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ ወልዋሎ ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡
የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች ጌታነህ ከበደ እና ሸምሰዲን መሐመድ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ወልዋሎ ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ቡልቻ ሹራ አስቆጥሯል፡፡…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ከኤቨርተን ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአንፊልድ ሮድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
ሊጉን በ70 ነጥብ እየመራ የሚገኘው ሊቨርፑል ከተከታዮቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት እና ወደ ዋንጫው የሚያደርገውን ጉዞ ለማጠናከር ይፋለማል።
በሁሉም ውድድር…