Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር የነሀስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ለሀገሯ የነሀስ ሜዳሊያ አምጥታለች። በውድድሩ ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼቤት ቀዳሚ ስትሆን ጣሊያናዊቷ ናዲያ ባቶቼሌቲ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡ ሌሎች ኢትዮጵያን ወክለው በውድድሩ የተሳተፉት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ አምስተኛ፣ አትሌት ፎትየን ተስፋይ ሰባተኛ እንዲሁም አትሌት ጽጌ ገብረሰላማ 22ኛ ደረጃን በመያዝ…
Read More...

አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች። በሶስተኛው ምድብ የተወዳደረችው አትሌቷ ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ነው ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለችው። በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው አትሌት ሳሮን በርሄ 9ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ…

በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሦስቱም ኢትዮጵያውያን ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሦስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል፡፡ በማጣሪያው የተሳፉት ጌትነት ዋለ፣ ለሜቻ ግርማ እና ሳሙኤል ፍሬው ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።

ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች በአሜሪካ ጎት ታለንት ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 የአሜሪካ ጎት ታለንት እየተወዳደሩ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቶማስ አለሙ እና ታምራት አያሌው ቲቲ ቦይስ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል። ቲቲ ቦይስ ከሌሎች 8 ተወዳዳሪዎች ጋር በመፋለም ነው 4 ተወዳዳሪዎች ብቻ ወዳለፉበት የፍጻሜ ውድድር የተቀላቀሉት፡፡ ኢትዮጵያውያኑ የሰርከስ…

ኢትዮጵያ የደመቀችበት የሄልሲንኪ የዓለም ሻምፒዮና ሲታወስ…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2025 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኋላ በጃፓን ቶኪዮ ጅማሮውን ያደርጋል፡፡ በርካታ አትሌቶችም የኢትዮጵያ ስም እንዲናኝ፣ ሰንደቋም በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያስቻሉ ቀደምት አትሌቶችን ፈለግ ተከትለው በሻምፒዮናው ላይ ለግል ስኬታቸው ብሎም ለሀገራቸው ክብር ይወዳደራሉ፡፡…

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተጠባቂ ጨዋታዎች ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሁለት ሳምንታት እረፍት በኋላ የማንቼስተር ደርቢን ጨምሮ በተጠባቂ የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች ይመለሳል፡፡ በ2026 የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ መርሐ ግብር ለየሀገራቸው ሲጫወቱ የሰነበቱ ተጫዋቾች ወደ ክለቦቻቸው ተመልሰዋል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገ ቀን 8፡30…

20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ በቶኪዮ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በነገው ዕለት በጃፓን ቶኪዮ ከተማ በይፋ ይጀመራል፡ ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከ800 ሜትር ጀምሮ እስከ ማራቶን ባሉ ርቀቶች እንዲሁም በእርምጃ ውድድር በሁለቱም ጾታ ትሳተፋለች፡፡ በውድድሩ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም በተለያየ ዙር ወደ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ አቅንተዋል፡፡…