ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ መቻል አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል አዳማ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የመቻልን የማሸነፊያ ግቦች ጳውሎስ መርጊያና በረከት ደስታ ከመረብ አሳርፈዋል።
ይህን ተከትሎም መቻል አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ከወላይታ ድቻ ጋር በነጥብ ተስተካክሎ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
Read More...
በኒው ዮርክ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ53ኛው የኒው ዮርክ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ሳይቀናቸው ቀረ።
በወንዶች ታምራት ቶላና አዲሱ ጎበና የተወዳደሩ ሲሆን አትሌት ታምራት ቶላ 2:08:12 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።
በተመሳሳይ በሴቶች ማራቶን አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ 2:27:14 በሆነ ሰዓት በመግባት 7ኛ ደረጃ…
ባህርዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት በመለያየት ነጥብ ተጋርተዋል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴ ታይቷል።
የፕሪሚየር ሊጉ የ7ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ…
በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ሲቲ ሲሸነፍ ሊቨርፑል አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ ሲሸነፍ ሊቨርፑል ድል ቀንቶታል፡፡
ወደ ቫይታሊቲ ስታዲየም ያቀናው የሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ በቦርንማውዝ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡
ለቦርንማውዝ ግቦቹን ሴሜኞ እና ኢቫኒልሰን ሲያስቆጥሩ÷ጆስኮ ግቫርዲዮል ደግሞ ሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ግብ…
አርሰናል በኒውካስል ዩናይትድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን የገጠመው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
የኒውካስል ዩናይትድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አሌክሳንደር ኢሳክ 12ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የጨዋታ መርሐ ግብሩ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አርሰናል ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን የሚገጥምበት ተጠባቂ ጨዋታ ቀን 9:30 ይደረጋል።
ምሽት 12:00 ላይ የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ በርንማውዝን የሚገጥም ሲሆን÷…
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በረከት ሳሙኤል (በራስ ላይ) እና ኢዮብ ገብረማርያም ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ሀዋሳ ከተማን ከሽንፈት…