Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ክሪስታል ፓላስ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ክሪስታል ፓላስ ሊቨርፑልን በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫን አሸንፏል። ከፍተኛ ፉክክር በታየበትና በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ሊቨርፑልን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል። ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ባደረጉት ፍልሚያ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ÷ የሊቨርፑልን ግቦች አዲስ ፈራሚዎቹ ሁጎ ኢኪቲኪ እና ጀረሚ ፍሪምፖንግ አስቆጥረዋል፡፡ የክሪስታል ፓላስን ሁለቱን ግቦች ማቴታ እና ኢስማኢል ሳር አስቆጥረዋል።…
Read More...

የኮሙዩኒቲ ሺልድ ፍፃሜ ጨዋታ…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ሊቨርፑል በኮሙዩኒቲ ሺልድ የፍፃሜ ጨዋታ ከኤፍኤ ዋንጫ አሸናፊ ክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል። በአርነ ስሎት የሚመሩት ሊቨርፑሎች በዌምብሌይ ስታዲየም ከክሪስታል ፓላስ ጋር የኮሙዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን ለማንሳት አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ይፋለማሉ። ማንቼስተር ሲቲን…

ከዩናይትድ መሰናበት እስከ ባሎንዶር ዕጩነት – ስኮት ማክቶሚናይ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ስኮትላዳዊው የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ስኮት ማክቶሚናይ ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር ከተለያየ በኋላ ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ ተጫዋቹ ባለፈው ክረምት ናፖሊን በተቀላቀለ በመጀመሪያ ዓመቱ የስኩዴቶውን ዋንጫ ከክለቡ ጋር ከማንሳት አልፎ በጣልያን ሴሪ አ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡…

ኦስማን ዴምቤሌ እና ላሚን ያማል ለባሎንዶር አሸናፊነት ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፒኤስጂው ኦስማን ዴምቤሌ እና የባርሴሎናው ላሚን ያማል ለባሎንዶር አሸናፊነት ይጠበቃሉ። በዛሬው ዕለት የ2025 የባሎንዶር፣ ኮፓ፣ ያሲን እና የአሰልጣኞች ሽልማት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በፈረንጆቹ መስከረም ወር በፓሪስ በሚካሄደው የ2025 የባሎንዶር እጩዎች ዝርዝር ይፋ ሲደረግ ኦስማን ዴምቤሌ፣ ላሚን ያማል እና…

ቪያሪያል የቶማስ ፓርቴን ዝውውር አጠናቀቀ

‎አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቪያሪያል የአርሰናል የመሀል ሜዳ ተጫዋች የነበረው የቶማስ ፓርቴን ዝውውር አጠናቅቋል። ቪያሪያል የ32 ዓመቱን የቀድሞ የመድፈኞች ተጫዋች ቶማስ ፓርቴ በነጻ ዝውውር የግሉ ማድረግ ችሏል። ጋናዊው ተጫዋች በነጻ ዝውውር የስፔኑን ክለብ የተቀላቀለ ሲሆን÷ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት መፈራረሙን ዘ አትሌቲክ…

ጀምስ ማዲሰን ለበርካታ ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቶተንሀም ሆትስፐር አማካይ ጀምስ ማዲሰን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አረጋግጧል፡፡ ተጫዋቹ ባጋጠመው ጉዳት ከስድስት እስከ ሰባት ወራት ከሜዳ ሊርቅ ይችላል ተብሏል፡፡ የ28 ዓመቱ እንግሊዛዊ ጉዳቱ ያጋጠመው ከቀናት በፊት ቶተንሃም ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ባደረገው የቅድመ ውድድር…

ቲሞቲ ዊሃ ማርሴን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ እግር ኳስ ኮከቡ ጆርጅ ዊሃ ልጅ ቲሞቲ ዊሃ የፈረንሳዩን ክለብ ኦሎምፒክ ደ ማርሴን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ቲሞቲ ዊሃ ከጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ወደ ኦሎምፒክ ደ ማርሴ አምርቷል፡፡ የ25 ዓመቱ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለጁቬንቱስ ባደረጋቸው 30 የጣሊያን ሴሪ…