Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እየተፈተነ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር በአዲስ አቀራረብ በሊግ ቅርፅ መደረግ ከጀመረ ወዲህ በመድረኩ እየተፈተነ ይገኛል፡፡ በ2024/25 የውድድር ዘመን ውድድሩ በአዲስ አቀራረብ መደረግ በጀመረበት ወቅት ሪያል ማድሪድ 16ቱን ለመቀላቀል የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አደርጎ 16ቱን የተቀላቀለው ሪያል ማድሪድ በመድረኩ መጓዝ የቻለው እስከ ሩብ ፍጻሜ ብቻ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በዚህኛው የውድድር ዓመትም ሪያል ማድሪድ 16ቱን…
Read More...

ሀገር አቀፍ የአዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና እና ምዘና ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የአዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና እና ምዘና ውድድር በስኬት ተጠናቅቋል። "የአዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ ከየካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የተካሄደው ውድድር…

ማንቼስተር ሲቲ ሳልፎርድ ሰቲን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ 4ኛ ዙር በተደረገ ጨዋታ ማንቼስተር ሰቲ ሳልፎርድ ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ዶሪንግተን (በራስ ላይ) እና ማርክ ጌሂ አስቆጥረዋል፡፡ በሌሎች ጨዋታዎች ዌስትሀም ዩናይትድ ቡርቶን አልቢዮንን 1 ለ 0 ፣ ኖርዊች ሲቲ ዌስትብሮሚች አልቢዮንን 3 ለ 1 እና…

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችን የማዘጋጀት ሙሉ አቅም እንዳላት ተመልክተናል – ፒርስ ኦክላጋን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችን የማዘጋጀት ሙሉ አቅም እንዳላት ተመልክተናል አሉ የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን፡፡ ፒርስ ኦክላጋን በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘውን የአደይ አበባ ዓለም አቀፍ የመለማመጃ ትራክና በመገባደድ ላይ የሚገኘውን ስታዲየም በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡…

ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ 5ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ ምሽት 5 ሰዓት 15 ላይ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡ በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ማንቼስተር ዩናይትድ 5ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡…

በእግር ኳስ ሕይወቱ 13ኛ ክለቡን የተቀላቀለው ሮድሪጌዝ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ2014 የብራዚል ዓለም ዋንጫ በኋላ በምርጥ ብቃቱ መቀጠል ያልቻለ ተጫዋች ነው ኮሎምቢያዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ፡፡ በፈረንጆቹ 1991 የተወለደው ሀሜስ ሮድሪጌዝ እግር ኳስን መጫወት የጀመረው በሀገሩ ክለብ ኢንቪጋዶ ነው፡፡ ከዚያ በመቀጠል በተለያዩ ሊጎችና ክለቦች መጫወት የቻለ ሲሆን የተጠበቀውን…

የሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) "ልውቅሽ ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት የሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ተካሂዷል። በውድድሩ በሴቶች አትሌት ቤተልሄም አስማረ እንዲሁም በወንዶች ስማቸው ወልዴ አሸንፈዋል። አትሌት ቤተልሄም አስማረ 1 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቅቃለች። አትሌት ትነበብ ነጋ እና…