ስፓርት
ሲዳማ ቡና እና መቻል አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ብለስ ናጎ ፣ ዮሴፍ ዮሀንስና ፍራኦል መንግሥቱ አስቆጥረዋል።
በሌላ በኩል መቻል ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ሁለቱንም የመቻልን ግቦች ፈቱዲን ጀማል ከመረብ አሳርፏል።
ቀደም ሲል በተደረገ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ድሬዳዋ ከተማ ያለምንም ግብ በአቻ…
Read More...
ኢትዮጵያ መድን እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ድሬዳዋ ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ መድን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች አቻ ሲለያይ ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ ያለፉትን…
ሀዋሳ ከተማ ነገሌ አርሲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ነገሌ አርሲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሀዋሳ ከተማን ግቦች ሽመልስ በቀለ እና ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ አሳርፈዋል።
ቀደም ብለው በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ምድረ ገነት…
ካፍ በአልጄሪያ ላይ የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት አስተላለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በአልጄሪያ ላይ የ100 ሺህ አሜሪካን ዶላር ቅጣት አስተላልፏል።
ቅጣቱ የተላለፈው አልጄሪያ እና ናይጄሪያ ባደረጉት የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የአልጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጨዋቾችና ደጋፊዎቻቸው ተገቢነት የሌለውን ባሕሪ በማሳየታቸው እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህም ግብ…
አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 ሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የአዳማ ከተማን ግቦች አህመድ ሁሴን (በፍጹም ቅጣት ምት)፣ ቢንያም አይተን እና አቡበከር ሳኒ አስቆጥረዋል።
አዲስ…
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ግብ ኮንኮኒ ሀፊዝ ሲያስቆጥር÷ ሄኖክ አዱኛ ደግሞ የሸገር ከተማን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
የሊጉ…
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዛሬ 9 ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
5 ሰዓት ማርሴ ከሊቨርፑል፣ ስላቪያ ፕራግ ከባርሴሎና፣ ባየር ሙኒክ ከሮያል ዩኒየን እንዲሁም ቼልሲ ከፓፎስ ይጫወታሉ።
በተመሳሳይ ሰዓት አትላንታ ከአትሌቲክ ቢልባኦ፣ ጁቬንቱስ ከቤኔፊካ እንዲሁም ኒውካስል ከፒኤስቪ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።…