Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ጆዜ ሞሪኒሆ የቤኔፊካ አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ አሰልጣኝ መሆናቸው ይፋ ሆነ። ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በቤኔፊካ እስከ ፈረንጆቹ 2027 የሚያቆያቸውን የሁለት ዓመት ኮንትራት ተፈራርመዋል። ሞሪኒሆ ከዚህ ቀደም ሪያል ማድሪድ፣ ኢንተር ሚላን፣ ቼልሲ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር እንዲሁም ፖርቶን የመሳሰሉ ክለቦችን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ነው። በቅርቡ ከቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ የተሰናበቱት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ኃላፊነት በመመለስ የቤኔፊካ አሰልጣኝ ሆነዋል። አሰልጣኙ በዚህ የውድድር ዓመት…
Read More...

ኢትዮጵያ በሴቶች የ3ሺህ ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች የ3ሺህ ሜትር መሰናክል በሲምቦ አለማየሁ አማካኝነት ተጨማሪ የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡ በርቀቱ ከአትሌት ሲምቦ አለማየሁ በተጨማሪ ኢትዮጵያን የወከለችው ሎሚ ሙለታ 8ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቅቃለች፡፡ ውድድሩን ኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ቼሮቲች በበላይነት…

በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ ገቢ ያገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 666 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ ገቢ ማግኘቱን ነው ቢቢሲ የዘገበው፡፡ ለአምስት ዓመታት ከማልያ ላይ ስፖንሰር ከሆነው ስናፕድራገን ጋር ያደረገው ስምምነት ክለቡ…

አርሰናል አትሌቲክ ቢልባኦን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል በሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ አትሌቲክ ቢልባኦን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ አርሰናል አትሌቲክ ቢልባኦን በሜዳው እና በደጋፊዎቹ ፊት ነው 2 ለ 0 ያሸነፈው፡፡ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ከባድ ፉክክር የገጠማቸው መድፈኞቹ ከእረፍት መልስ ተቀይረው የገቡት ማርቲኔሊ…

ፈላጊ ክለብ ያጣው ዴሊ አሊ…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአንድ ወቅት የዝውውር ሒሳቡ ወደ 100 ሚሊየን ዩሮ ከፍ ብሎ የነበረው እንግሊዛዊው ተጫዋች ዴሊ አሊ አሁን ፈላጊ ክለብ ለማግኘት ተቸግሯል፡፡ የ29 ዓመቱ የቶተንሃም የቀድሞ ተጫዋች ዴሊ አሊ በተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ቢያሳልፍም አሁን እሱን ለማስፈረም ፍላጎት ያለው ክለብ ሊገኝ አልቻለም፡፡ የሕይወት አጋጣሚ…

ኢትዮጵያ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር የብር ሜዳልያ አገኘች። ብርቱ ፉክክር በታየበት በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ በመውጣት ነው ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የብር ሜዳልያን ያስገኘው። በውድድሩ ላይ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን በ6ኛነት…

አትሌት ፍሬወይኒ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ለፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ለፍጻሜ አለፈች። በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በተደረገው ማጣሪያ የምድቡ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ ማለፍ ችለዋል። አትሌት ፍሬወይኒ በምድብ አንድ ባደረገችው ውድድር 4 ደቂቃ ከ1 ሴኮንድ…