ስፓርት
ሞሐመድ ሳለህ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኗል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብጻዊው የሊቨርፑል ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ በእግር ኳስ ፀሐፊዎች ማኅበር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ሳላህ በውድድር ዓመቱ 28 ግቦችን በማስቆጠርና 18 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ሊቨርፑል የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ እንዲሆን አስችሏል፡፡
በተጨማሪም በአንድ የውድድር ዓመት ብዙ የጎል ተሳትፎ ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችሏል፡፡
ሊቨርፑል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 16ቱን እንዲቀላቀል 3 ጎሎችን በማስቆጠር እና 4 የግብ ኳሶችን በማቀበል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡…
Read More...
ሐዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ታፈሰ ሰለሞን በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሐዋሳ ከተማ ወደ ድል ሲመለስ ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ውጤቱን ተከትሎም…
ማንቼስተር ዩናይትድ ከአትሌቲክ ቢልባኦ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ምሽት 4 ሠዓት ላይ አትሌቲክ ቢልባኦን ያስተናግዳል።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ስፔን አቅንቶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
በሌላ በኩል ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ መጨረሻ በየሊጋቸው ባደረጉት ጨዋታ ድል…
ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግቦች ሙሉቀን አዲሱ እና ካርሎስ ዳምጠው ሲያስቆጥሩ፤ የአርባምንጭ ከተማን ብቸኛ ጎል አህመድ ሁሴን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ወላይታ ድቻ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ሲመለስ…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ላይ የሜዳ እና የሰዓት ለውጥ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀዋሳ ከተማ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀሪ 4 ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳ እና የሰዓት ለውጥ መደረጉን የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ አሳወቀ።
ጨዋታዎቹን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለማካሄድ መርሐ ግብር የወጣ ቢሆንም እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የሰዓት እና…
ፒኤስጂ ከአርሰናል ለሙኒኩ ፍጻሜ….
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ በሜዳው ፓርክ ደ ፕሪንስ ዛሬ ምሸት 4 ሰዓት ላይ አርሰናልን ያስተናግዳል።
የዛሬ ምሽት የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ቡድኖች በታሪካቸው አንድም ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሳክተው አያውቁም።
ሁለቱ ቡድኖች ኤሚሬትስ ላይ ባደረጉት…
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ ግብ አማኑኤል ኤርቦ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ቀን 9 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልዋሎ ዓዲግራት…